በ2018 ይሰራጫል ከተባለው 6 ሚሊዮን ኮንዶም ግማሽ የሚሆነው ጁቡቲ ደርሷል ተባለ
ኮንዶሞችን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ለተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚያቀርበው ኤድስ ሄልዝ ኬር ፋውንዴሽን በተያዘው ዓመት ለማስገባት ከታቀደው 6 ሚሊዮን ኮንዶም ግማሽ ያህሉ ጅቡቲ መድረሱን የኤድስ ሄልዝ ኬር ፋውንዴሽን የኤች አይ ቪ መከላከያ የአፍላ ህይወት አድቮኬሲ ኃላፊ የሆኑት አቶ ቶሎሳ ኦላና ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት ብስራት ሬዲዮ በሰራው ዘገባ በየዓመቱ ከሶስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኮንዶም ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት እና በነጻ እየተከፋፋለ እንደሚገኝ እና በ2018 ዓመት ደግሞ 6 ሚሊዮን ኮንዶም በነጻ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ መዘገቡ ይታወሳል።
በመሆኑም ብስራት ሬዲዮ ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገባው የኮንዶም አቅርቦት በምን መልኩ ነው ተደራሽ የሚሆነው የሚል ጥያቄ አቅርቧል፤ በዚህም ስርጭቱ ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ የጤና ተቋማት ተደራሽ ያደረገ መሆኑን እና ድጋፍ እንዲደረግላቸው በደብዳቤ ላቀረቡ ድርጅቶች ቅድሚያ እንደሚሰጥ አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም ከፌደራል ፖሊስ፣ ከመከላከያ በስፋት የሚመጡ ጥያቄዎች በመኖራቸው ቅድሚያ ተደራሽ እንደሚሆኑ አክለዋል። በሁለት ዙር እንደሚገባ እና በአሁን ሰዓት 2.5 እስከ 3 ሚሊዮን የሚሆነው ጅቡቲ መድረሱን በማንሳት በሚገባ ተደራሽ መሆን ላለበት አካል ለማቅረብ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አቶ ቶሎሳ ኦላና ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.