ግብፅ የቴክኒክ ባለሙያዎቿን ወደ ኤርትራ ልትልክ ነው!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ግብፅ እና ኤርትራ በኢንዱስትሪ እና በመሰረተ ልማት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል ስምምነት ላይ ደረሱ። በካይሮ በተካሄደው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ውይይት፣ ግብፅ ያላትን የኢንዱስትሪ ተሞክሮ ለኤርትራ ለማካፈል ቁርጠኝነቷን ገልጻለች።
የስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

በኤርትራ ለሚከናወኑ የኢንዱስትሪ እና የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የሚውሉ የቴክኒክ ባለሙያዎችን ለማሰማራት ተዘጋጅታለች።

የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚረዱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ማዕከላት በኤርትራ ይገነባሉ።

ልታዊ የሆኑ ፋብሪካዎችን እና የመሠረተ ልማት አውታሮችን ለመገንባት የሚያስችሉ ዝርዝር ጥናቶች በግብፅ ባለሙያዎች አማካኝነት ይከናወናሉ።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እንቅፋቶች በመቅረፍ በቀይ ባሕር ቀጣና ጠንካራ የኢኮኖሚ ትስስር ለመፍጠር ታቅዷል።

ይህ እንቅስቃሴ ግብፅ በአፍሪካ ቀንድና በቀይ ባሕር ቀጣና ያላትን ተፅዕኖ ለማሳደግና ከኤርትራ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ አጋርነት ለመለወጥ የምታደርገው ጥረት አካል ተደርጎ ተወስዷል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#capital #getutemesgen #getu
#ግብፅ #ኤርትራ #ኢንዱስትሪ #ኢኮኖሚ #የቀይባሕር #ዜና #LeadThePlot


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: