ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች በእስራኤል ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠየቁ።የፈረንሳይ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ማኖን ኦብሪ እንዳስታወ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች በእስራኤል ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠየቁ።
የፈረንሳይ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ማኖን ኦብሪ እንዳስታወቁት ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የአውሮፓ ህብረት ዜጎች በእስራኤል ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቅ ፒቲሽን(አቤቱታ)በይፋ ፈርመዋል።
ይህ ቁጥር በአውሮፓ ህብረት ህግ መሰረት የአውሮፓ ኮሚሽን እና የአውሮፓ ፓርላማ የዜጎቹን ጥያቄ በግዴታ እንዲገመግሙ እና ምላሽ እንዲሰጡ ያስገድዳል።
የአውሮፓ ዜጎች ይህን ፒቲሽን ያዘጋጁት እስራኤል በጋዛ ለምትፈጽማቸው ድርጊቶች ተጠያቂ እንድትሆን ነው።
የዜጎቹ ዋና ጥያቄ በአውሮፓ ህብረት እና በእስራኤል መካከል ያለውን የሁለትዮሽ የንግድ እና የፖለቲካ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ማገድ ነው።ይህን ማገድ በኢኮኖሚ እና በዲፕሎማሲ ረገድ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል።
እስራኤል በጋዛ ንጹሃን ዜጎች ላይ ላደረሰችው የሞት፣የአካል ጉዳት እና የጅምላ ማፈናቀል ህጋዊ ተጠያቂ እንድትሆን አጥብቀው ይጠይቃሉ።
ሆስፒታሎችን፣ የህክምና ተቋማትን እና መሠረተ ልማቶችን ማውደም በአለም አቀፍ ህግ መሰረት የጦር ወንጀል እንደመሆኑ ይህ ድርጊት እንዲቆም እና ለፈጸሙት ድርጊት እንዲቀጡም ጠይቀዋል።
በአጠቃላይም ህብረቱ ከእስራኤል ጋር ያለውን ግንኙነት እንደገና እንዲገመግም እና የሰዎች መብት በሚጣስበት ጊዜ ዝምታን መምረጥ እንደማይገባ የገለጹ ሲሆን ይህም በህብረቱ ውጫዊ ግንኙነት ላይ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
እነዚህ አንድ ሚሊዮን ፊርማዎች ለህብረቱ አመራሮች የዜጎችን ስሜት የሚያንጸባርቁ የማንቂያ ደወል ናቸው። ህብረቱ ለዜጎቹ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጥ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ግንኙነቱን እስከ ምን ደረጃ ድረስ እንደሚቀንስ ብሎም እስራኤልን ምን ያህል እንደሚያርማት መላው አለም በጉጉት ይጠባበቃል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: