የተነሣው፡፡ እሱን ሞት ሊይዘው ቀርቶ ሊቀርበው አይችልም፡፡ ነገር ግን የትንሣኤያችን በኵር ለመኾን ለአርአያነት፣ ለቤዛነት እሱ

- Advertisement -
Sidebar AD

የተነሣው፡፡ እሱን ሞት ሊይዘው ቀርቶ ሊቀርበው አይችልም፡፡ ነገር ግን የትንሣኤያችን በኵር ለመኾን ለአርአያነት፣ ለቤዛነት እሱ ተበድሎ እኛን ለማዳን እሱ ካሰን፡፡ የተበደለውም የካሰውም እሱ ነው፡፡

በዚህ ዕለትም ትንሣኤ ልቦናን እና በኋላ በዳግም ምጽአት የምንነሣውን ትንሣኤ ዘጉባኤን እናስባለን፡፡ ዳግም ትንሣኤ ሌላ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት፡፡ እነዚህም ፈጸምነ፣ አግብኦተ ግብር ይባላሉ፡፡

ፈጸምነ
“ፈጸምነ” ማለት ከእሑድ እስከ እሑድ ስለ አንድ ቀን ይቆጠራል፡፡ ፈጸምነ የተባለበትም የበዓሉን ቀን (የሰሙነ ትንሣኤን) በዓል አክብረን ጨረስን፣ ፈጸምን ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩልም የተነገረው ትንቢት፣ የተመሰለው ምሳሌ አለቀ፣ ተፈጸመ ለማለት ነው፡፡ እንዲሁም ጌታችን የሰውነት ሥራውን ሲያከናውን ከቆየ በኋላ በፍጻሜ አካባቢ ለባሕርይ አባቱ ባቀረበው ጸሎት “እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ፈጽሜ በምድር አከበርኩህ” በማለት የጸለየውን አምላካዊ ጸሎት በተወሰነ ቀን ፈጸምነ ብለውታል /ዮሐ.፲፯÷፬/፡፡ በዚህ ቀን ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በዝግ ቤት ሳሉ በር ሳይከፈት ገብቶ በመካከላቸው በመገኘት ሰላም ለሁላችሁ ይሁን የአለበት ቀን ነው፡፡ ይህም ክርስቶስ የመጣበትን ዓላማ መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ስም አጠራር ነው፡፡ በአጠቃላይ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣበትን ዓላማ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ሰዎችን ከኃጢአት ነጻ ለማውጣት በሞቱም ዘለዓለማዊ ሕይወትን ሰጥቶ፣ በትንሣኤው ለትንሣኤያችን በኵር ለመኾን በመኾኑም ይህንኑ ሥራውን ያጠናቀቀ መኾኑን ለማመልከት ነው፡፡

አግብኦተ ግብር
አግብኦተ ግብር (የግብር ማግባት) የኤማሁስን ማዕድ ነው፤ ግብር ማዕድ ማለት ነው፡፡ በማዕድ ተሰብስበው እንዳሉ ተገለጸላቸው /ሊቃ.፳፬÷፲፫/፡፡ “አግብኦተ ግብር” የተባለበትም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እኔ ልሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጸምኩ” ያለውን ከቅዳሴ በኋላ ሊቃውንት በዚህ ቀን ስለሚዘምሩት የተሰጠው ስያሜ ነው፡፡ ምስጢሩ ግን ሥጋ የተገዢነት ሥራ ፈጸመ፡፡ ከእንግዲህ በአብ እሪና ተቀምጦ ይፈርዳል ለማለት ነው፡፡ /ዮሐ. ፲፯÷፬/፡፡

እንደ ማጠቃለያ

በአጠቃላይ በቅድስት ቤተክርስቲያን በሰሙነ ትንሣኤ የሚፈጸመው መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ሁሉ ልክ እንደ መጀመሪያው የትንሣኤ ሥርዐት ኾኖ ይከናወናል፡፡ በማኅበራዊ ኑሮም የፋሲካ ሳምንት ብዙ መንፈሳዊና ባሕላዊ ቁምነገሮች የሚፈጸሙበት ሳምንት ነው፡፡ ወገን ከወገን የሚገናኝበት፣ ጎረቤት ከጎረቤት ተጠራርቶ የሚገባበዝበት፣ ካህናትና ምእመናን በአንድነት ተገናኝተው መታሰቢያውን የሚያከብሩበት፣ የተጣላ የሚታረቅበት፣ ጋብቻ ከጋብቻ ተጠራርቶ የሚገናኝበት፣ የሚገባበዙበት በጠቅላላው ሰላም የሰፈነበት መልካም የዕረፍት ሳምንት ነው፡፡

ለብርሃነ ትንሣኤው ያደረሰን አምላካችን ለብርሃነ ዕርገቱም በሰላም ያድርሰን፡፡ አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ዋቤ መጻሕፍት
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ ፍትሐ ነገሥት
✍️ ሃይማኖት አበው
✍️ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ
✍️ ከስቅለት እስከ ትንሣኤ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2