ሸይህ ሰልማን አወል አማን ወደ አኼራ ተሻገሩ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ላለፉት 50 ዓመታት ማሕበረሰብን በሁለንተናዊ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት አንጋፋው አሊም ሸይህ ሰልማን አወል በትላንትናው ዕለት ወደ አኼራ መሻገራቸው ተሰምቷል።

​ሸይህ ሰልማን ከመሃል ከተማ እስከ ተለያዩ ክልሎች የገጠር ክፍል ድረስ አንጸባራቂ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

​ከቅርብ ወዳጆቻቸው ጋር ሆነው ከ20 በላይ የጁምዓ መስጂዶች፣ የቁርኣን ሒፍዝ ማዕከላት፣ አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲመሠረቱ አስችለዋል።

​በገጠሩ ክፍል የተንሰራፋውን የግንዛቤ ክፍተት እና የዕውቀት ውስንነት ለመቅረፍም ከፍተኛ የአስተማሪነት ትግል አካሂደዋል።

​በርካታ ተተኪ ልጆችን፣ ዓሊሞችን፣ ተማሪዎችን ያፈሩት ሸኽ ሰልማን በትናንትናው ዕለት ወደ አኼራ እንደተሻገሩ ተገልጿል ሲል ሀሩን ሚዲያ ዘግቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1