በጠቅላላ ጉባኤው ከተነሱ ውሃ የሚያነሱ ሃሳቦች

- Advertisement -
Sidebar AD

📌

👉 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ቢኒያም ምሩፅ በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ከተናገሩት የተወሠደ

♦️”የሚኒስቴር መ/ቤቱን ውለታ በልተናል፤ከማንም በላይ መመስገን ያለበት ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ነው”

♦️”እኛ(አሁን ያለው ስራ አስፈፃሚዎች)ዕድለኞች ነው፤በሶስት ወር ውስጥ ሁለት ትራክ በእነሱ አመራር ነው ያገኘነው”

♦️”ከእኛ በላይ መመስገን ያለበት ሚኒስትር መ/ቤቱ ነው፤እኛን አንድንሠራ መርጣችሁናል፤መመስገን የለብንም ምክንያቱም ስራችን ነው”

አቶ ቢኒያም ምሩፅ
(የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል)

#Ethiopia | የሚኒስቴር መ/ቤቱን ውለታ በልተናል፤ከማንም በላይ መመስገን ያለበት ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ነው፤ ክብርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካና በተለይም የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የተከበሩ አቶ መኪዩ መሀመድ ከማናችንም በላይ በጣም መመስገን አለባቸው።

እኛ(አሁን ያለው ስራ አስፈፃሚ)ዕድለኞች ነው፤በሶስት ወር ውስጥ ሁለት ትራክ በእነሱ አመራር ነው ያገኘነው፤ክብርት ሚኒስትራ በግራንድ ፕሪ አዲስ 2026 ዙሪያ ከአንዴም ሁለቴ አወያይተውናል፤ከጎናችን ሆነዋል፣ሜዳ ድረስ መጥተው ጎብኝተውናል፤

በተለይ ደግሞ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ መኪዩ መሀመድ በቀን ሁለቴ ሶስት እስከ ምሽት ድረስ አብረውን እያመሹ፣አብረውን እየሠሩ፣እየገመገሙ ይሄንን ታሪካዊ ውድድር እንድናዘጋጅ አድርገውናል፤ ከ60 እና 70 ፐርሠንት በላይ ሠርተዋል ብዬ ስለማምን ከእኛ በላይ መመስገን ያለበት ሚኒስትር መ/ቤቱ ነው፤እኛን አንድንሠራ መርጣችሁናል፤መመስገን የለብንም ምክንያቱም ስራችን ነው።ፕሬዝዳንቱ፣ስራ አስፈፃሚው፣ፅ/ቤቱም ምስጋና ቢገባቸውም ሚኒስትር መ/ቤቱ በተለይ ሁለቱ የስፖርቱ ከፍተኛ መሪዎች በጣም መመስገን አለባቸው”

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: