የዳኝነት ስርዓትን ለማዘመን እየተሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የቤልጅየም አባሳደር ገለጹ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮጵያ የቤልጂየም አምባሳደር እና የአፍሪካ ሕብረት ቋሚ ተወካይ ክብርት ዶ/ር አኔሊስ ቨርስቲሸል በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አምባሳደሯን ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን፤ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓትን ለማዘመን እየሰራ ያለውን ስራ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

በውይይታቸው የልምድ ልውውጦችን ለማድረግ እና አጋርነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ንግግሮች አካሂደዋል፡፡

እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓትን ለማዘመን እየሰራቸው ያሉ የዲጂታላይዜሽን ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በፍርድ ቤቱ እየተተገበሩ የሚገኙ የቴክኖሎጂ ስራዎችን ተዘዋውረው የጎበኙት አምባሳደሯ፤ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓትን ለማዘመን እየሰራቸው ያሉ የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ልምድ የሚወሰድባቸውና የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት

Belgium’s Ambassador Praises Ethiopia’s Efforts to Modernize Judicial System

Belgium’s Ambassador to Ethiopia and Permanent Representative to the African Union, H.E. Dr. Annelies Verstichel, visits the Federal Supreme Court to discuss various issues.

H.E. Mr. Tewodros Mihret, The president of the Federal Supreme Court of Ethiopia receives the ambassador for a discussion. During the meeting, the president provides a detailed briefing on the Federal Supreme Court’s ongoing efforts to modernize the judicial system.

The talk holds on ways to facilitate experience sharing and strengthen partnerships, particularly in the context of implementing digital tools and best practices in judicial services delivery.

Following the meeting, the ambassador conducts a field visit to observe the digitalization projects currently used by the Federal Supreme Court to modernize the judicial system.

The ambassador describes the digitalization efforts of the Federal Supreme Court as admirable and exemplary. During her tour, she observes how the court is integrating new technology to simplify its judicial service delivery.

Federal Supreme Court)






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2