የጥበብ ዓምዱ አታኽልቲ ነጋ በአዲስ ስራ ተመለሰ

- Advertisement -
Sidebar AD

* “ውሽጥን ደገን” ሊመረቅ ነው

#Ethiopia | ​ከሦስት አስርተ ዓመታት በላይ በትግራይ የፊልምና ድራማ ዘርፍ ላይ የማይደበዝዝ አሻራ ያሳረፈው፣ መምህር፣ ደራሲና ተዋናይ አታኽልቲ ነጋ ዳግም ወደ ስክሪን ተመልሷል።

በ”ማሾ” እና “ምትሓታዊ ዓለባ” (ብርሆን ገይፀን) የብዙዎችን ልብ የገዛው ይህ የጥበብ ሰው፣ አሁን ደግሞ “ውሽጥን ደገን” (Inside/Outside) በተሰኘ አዲስ የሲትኮም ድራማ ብቅ ብሏል።

​ቀን፦
እሁድ ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት።

​ቦታ፦
በመቀለ ሰማዕታት ሐውልት በሚገኘው ሲኒማ አዳራሽ።

​ በሸባ ኢንተርተይመንት አዘጋጅነት የቀረበ ሲሆን፣ በቅርቡ በትግራይ ቴሌቪዥን በሳምንት ሦስት ጊዜ ለተመልካች ይደርሳል።

አታኽልቲ ነጋ “ያለ ግንድ ቅርንጫፍ የለም” የሚለውን አባባል በተግባር ያሳየ፣ ለብዙ ወጣት ባለሙያዎች ፈር ቀዳጅ የሆነ የጥበብ መምህር ነው። ይህ አዲስ ስራው የቀድሞውን ጣፋጭ የትግርኛ ድራማ ለዛ ይዞ እንደሚመጣ ጥርጥር የለውም። ሁላችሁም እሁድ በመቐለ በመገኘት ይህንን የጥበብ ጀግና እንድታበረታቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

​(Trailer) ለማየት፦ እዚህ ይጫኑ

​ጥበብን በባለቤቱ፣ ታሪክን በፈጣሪው!

ብቸኛ አዘጋጅ
( Exclusive producer ) ሸባ ኢንተርተይመንት
በክብሮም ገ/መስቀል

የዚህን ተከታታይ ድራማ ማስተዋወቂያ (Trailer) ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://youtu.be/T6zFaqse64o

​#getu #AtakltiNega #TigrayFilm #WishtinDegen #ShebaEntertainment #TigrinyaDrama #EthiopianArt #Mekelle #InsideOutside #አታኽልቲነጋ #መቀሌ #ጥበብ #ትግርኛፊልም #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: