ወ/ሮ አሸነፈች አበበ የኢሰመኮ ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

- Advertisement -
Sidebar AD

​በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ በታማኝነትና በብቃት የሚታወቁት ክብርት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ፣ በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ዘርፍ ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

ላለፉት 6 ዓመታት በላይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን በከፍተኛ ኃላፊነት አገልግለዋል።

​በኢሰመኮ የሴቶችና ህፃናት መብት ጥበቃ ዘርፍን በኮሚሽነርነት ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንቱ የተሰማውን ደስታ እየገለጸ፣ የተሳካ የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።

ወ/ሮ አሸነፈች ያላቸው የዳኝነትና የአመራር ልምድ፣ በሀገራችን የሴቶችና የህፃናት መብት ይበልጥ እንዲከበርና የፍትህ ተደራሽነት እንዲሰፋ ለማድረግ ትልቅ ሚና ይኖረዋል። እንዲህ ያሉ ብቁ ሴት አመራሮች ወደ ቁልፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት መምጣታቸው ለሀገራችን የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ትልቅ ፋይዳ አለው።

​ለክብርት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ እንኳን ደስ አለዎት!

​#getu #BreakingNews #Appointment #EHRC #Ethiopia #HumanRights #WomenAndChildren #JusticeSystem #ኢሰመኮ #ሹመት #ሰብዓዊመብት #ፍትህ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: