”ኢራንን አንተካም!” — ጣልያን

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ፊፋ ኢራንን ከዓለም ዋንጫ አስወግዶ በምትኳ ጣልያንን እንዲያስገባ ያቀረቡት ጥያቄ በራሷ በጣልያን መንግሥትና በስፖርት አመራሮቹ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው።

​የጣልያን ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ሉቺያኖ ቦንፊግልዮ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ጠንከር ያለ ምላሽ፣ ጣልያን በሜዳ ላይ ባላሳየችው ውጤት በፖለቲካዊ መንገድ ወደ ዓለም ዋንጫ እንድትገባ የቀረበውን ሐሳብ እንደማይቀበሉት ገልጸዋል።

“ይሄ ከተፈጠረ እንደ ስድብ ነው የምወስደው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ማንኛውም ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማለፍ ያለበት በችሎታውና በጠንካራ ሥራው መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

​የሀገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም የኦሎምፒክ ኮሚቴውን አቋም ተጋርተዋል፦

​ “ይሄ አስፈላጊ አይደለም፤ ሜዳ ላይ ነው ማለፍ ያለብን” በማለት በጓሮ በር ወደ ውድድሩ የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው አስታውቀዋል።

​የኢኮኖሚ ሚኒስትር ጂዮርጌቲ፦ ዜናው በግላቸው እንዳሳፈራቸው ገልጸው፣ “በዛ መንገድ ከሄድን አፍራለሁ” ሲሉ የሐሳቡን አሳፋሪነት ገልጸዋል።

​ምንም እንኳን የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ለ2026ቱ ዓለም ዋንጫ ባለማለፉ ደጋፊዎቿ ቢያዝኑም፣ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ግን ከውጤት ይልቅ ለስፖርታዊ ጨዋነትና ለፍትሐዊ ውድድር ቅድሚያ በመስጠት ዓለም አቀፍ አድናቆትን እያገኙ ይገኛሉ።

ጣልያን “በችሎታችን ካላለፍን በሌላው ስንብት አንገባም” የሚል ጠንካራ መልዕክት ለዓለም አስተላልፋለች።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#Italy #FIFA #WorldCup2026 #Iran #FootballNews #Sportsmanship #FairPlay #Azzurri #LucianoBonfiglio #AndreaAbodi #WorldCupUpdate


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: