#Ethiopia | የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሳካ ወደ ልምምድ መመለሱ ለቡድኑ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ገልጸዋል። ኮከቡ በካራባኦ ዋንጫ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ከተደረገው ጨዋታ ጀምሮ በጉዳት ምክንያት ከሜዳ ርቆ የቆየ ቢሆንም፣ አሁን ግን ለጨዋታ ዝግጁ መሆኑን አሰልጣኙ አረጋግጠዋል።
አርቴታ ”ለሳካ ትክክለኛውን የእረፍት እና የህክምና ጊዜ ሰጥተነዋል። አሁን ግን ቡድኑ በከፍተኛ ሁኔታ ይፈልገዋል፤ መመለሱም ለእኛ መልካም ዜና ነው” ብለዋል።
ምንም እንኳን ሳካ በዚህ የውድድር ዘመን በሁለት የተለያዩ ጉዳቶች ቢፈተንም፣ ካለፉት 32 የሊግ ጨዋታዎች በ27ቱ ላይ በመሰለፍ የቡድኑ የጀርባ አጥንት መሆኑን አስመስክሯል።
የሌሎች ተጫዋቾች ሁኔታ
ሪካርዶ ካላፊዮሪ፦ ጣሊያናዊው ተከላካይ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር ከተደረገው ጨዋታ በኋላ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ተነግሯል።
ጁሪየን ቲምበር፦ ለደጋፊዎች ጥቂት የማይዋጥ ዜና፣ ኔዘርላንዳዊው ተከላካይ ቲምበር አሁንም ከጉዳቱ ባለማገገሙ የነገው ጨዋታ እንደሚያመልጠው ታውቋል። ቲምበር ካለፉት ሰባት ጨዋታዎች ውጪ መሆኑ ይታወሳል።
አርሰናል ዛሬ ምሽት 1:30 ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ኒውካስልን ያስተናግዳል። ይህ ጨዋታ ለመድፈኞቹ እጅግ ወሳኝ ነው፤ ጨዋታውን ማሸነፍ ከቻሉ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ዳግም ለመረከብ ትልቅ እድል ይፈጥርላቸዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#NBCEthiopia #Ethiopia #Arsenal #PremierLeague #BukayoSaka #MikelArteta #COYG
Source: GetuTemesgen









No comments yet.