ለደንበኞች እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የዋጋ ቅናሽ ያደረገበት ሪል ስቴት ኤክስፖ ተከፈተ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja I አልቲማ ሪል እስቴት (Ultima Real Estate) በአዲስ አበባ ከተማ ያስገነባውንና ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀውን ባለ 12 ፎቅ (G+12) ዘመናዊ የመኖሪያ ህንፃ ለደንበኞች ማስረከብ መጀመሩን በዛሬዉ እለት አስታወቀ።

ድርጅቱ የርክክብ መርሃ-ግብሩን በማስመልከትም አዲስ የሪል እስቴት ኤክስፖ እና የሽያጭ ሳምንት በዛሬው ዕለት ከፍቷል።

ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሊምፒያ በሚወስደው መንገድ፣ ቱሊፕ ሆቴል ጀርባ የሚገኘው ይህ ሁለገብ የመኖሪያ ህንፃ ግንባታው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ነው ለባለቤቶቹ ርክክብ እየተደረገ የሚገኘው፡፡

ህንፃው አስተማማኝ የመኪና ማቆሚያ፣ የከርሰ ምድር ውሃ፣ የኤሌክትሪክ ጀነሬተር እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች የተሟሉለት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት አልቲማ ሪል እስቴት ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ገንብቶ ያስረከበው ሁለተኛው ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑ ተጠቁሟል።

የሪል እስቴት ድርጅቱ የርክክብ ስነ-ስርዓቱን አስመልክቶ በቱሊፕ ሆቴል አጠገብ የአምስት ቀን የሽያጭ ኤክስፖ የከፈተ ሲሆን፣ ኤክስፖው ከዛሬ ሚያዝያ 17 ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ አምስት ቀናት እንደሚቆይ ነዉ የተገለፀዉ።

በኤክስፖው መክፈቻ ላይ የአልቲማ ሪል ስቴት መስራች እና ባለቤት ኢንጂነር ዮሴፍ ፍቃዱ እንደገለጹት፣ በኤክስፖው ወቅት ቤቶችን ለመግዛት ለሚመዘገቡ ደንበኞች ለእያንዳንዱ ቤት እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ልዩ የዋጋ ቅናሽ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

መርሃ-ግብሩ “ፕሪሚየም ሳይት” (Premium Site) የተባለውን አራተኛውን አዲስ ፕሮጀክት ለደንበኞች ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።በተጨማሪም አዲስ ለሚጀመረው የመስቀል ፍላወር ፕሪሚየም ሳይት ፕሮጀክት ደንበኞች ከ5 በመቶ ቅድመ ክፍያ ጀምሮ መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ይህንን የሽያጭ መርሃ-ግብር ከአልቲማ ሪል እስቴት ጋር በመተባበር አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር (Arki Event Organizer) እያስተባበረው የሚገኝ ሲሆን አልቲማ ሪል እስቴት ከዚህ ቀደም የመጀመሪያ ፕሮጀክቱን በላንቻ አርባ ምንጭ ሳውና ቤት ፊት ለፊት ገንብቶ ማጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ያስረከበው ህንፃ በኩባንያው ታሪክ ሁለተኛው የተሳካ ርክክብ መሆኑ ተገልጿል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: