ለቀድሞ የስፖርት ባልደረቦች መታሰቢያ የሚሆን የእግር ኳስ ውድድር ተካሄደ

- Advertisement -
Sidebar AD

​በ1970 እና 1975 ዓ.ም መካከል በከፍተኛ 23 ቀበሌ 09 የእግር ኳስ ቡድን ውስጥ በጋራ ያሳለፉ አብሮ አደጎች፣ አሁን በሕይወት የሌሉ የቡድን መሪዎችንና ተጫዋቾችን ለመዘከር የታለመ ልዩ መርሐ ግብር አካሄዱ።

​ክብርና መታሰቢያ ለታታሪ የስፖርት ቤተሰቦች
​ይህ የውድድርና የመታሰቢያ መርሐ ግብር በዋናነት የተዘጋጀው የሚከተሉትን ባለውለታዎች በክብር ለማሰብ ነው ​ከቡድኑ አመራሮችና አሰልጣኞች
​አቶ ጌታቸው ወርቄ (የቡድን መሪ)፣ ​አስር አለቃ በቀለ እሽቴ (የቡድኑ ወጌሻ) ​ከቡድኑ ተጫዋቾች ​ደጀን ሀጎስ፣​እስጢፋኖስ ሀብቴ፣​ልዕል ገብረህይወት ፣​ግርማ መገርሳ፣ ​ወንድሙ አንጌቻ፣ ​ሰለሞን አባተ፣ ​አበበ ዘውዴ እና ​ሰመረ ደበሳይ ሲሆን ​በዕለቱም አስማማው ጥጋቡ ክብረት እና ሌሎች የቀድሞ የቡድን አባላት በመገኘት እነዚህን ስፖርተኞች በቤተሰቦቻቸው ተወክለው እንዲታሰቡ አድርገዋል።

​አዘጋጆቹ እንደገለጹት ይህ መርሐ ግብር ያለፈውን ከማሰብ ባለፈ የወደፊት ትልቅ ዓላማ አለው። ይህም አሁን በሕይወት ያሉ ወንድምና እህቶችን በጋራ ለማገዝ ታስቦ እየተቋቋመ የሚገኘው “የቀበሌ 09 ነዋሪዎች ህብረት” መሠረት እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

​ለስፖርቱ መነቃቃትና ለአዲሱ ትውልድ ማበረታቻ እንዲሆን ከከፍተኛ 23 ቀበሌ 09 ነባር ቡድን ለቄራ 09 የጤና ስፖርት ቡድን የ20 ቁምጣና ማልያ እንዲሁም የኳስ ስጦታ ተበርክቷል።

​በመጨረሻም በነባር ተጫዋቾችና በጤና ቡድኑ መካከል በተደረገው ጨዋታ፣ መደበኛው ሰዓት 3 ለ 3 በሆነ ውጤት ተጠናቆ በመለያ ምት የቀድሞው ከፍተኛ 23 ቀበሌ 09 ቡድን አሸንፎ ዋንጫውን አንስቷል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: