የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ረድኤቱ እና ምልጃው አይለየን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የዙፋን መልእክተኛ ነውና መልአክ ወይም መልእክተኛ ይባላል፡፡

ዳግመኛም በቅድስናው ቅዱስ ይባላል፡፡ ገብርኤል ማለት አምላክ ሰው ሆነ፣ ሰው አምላክ ሆነ” ማለት ነው፡፡ የሠራዊት አዛዥ ነውና ሊቀ መላእክት ይባላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል አብሳሬ ትስብዕት ነው፡፡ እመቤታችን አምላክን እንደምትወልድ ታላቁን የምሥራች ይዞ የደረሰው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ የሰው ልጆችን መዳን ታላቁን የምሥራች ይዞ በመምጣቱ መጋቤ ሐዲስ ይባላል፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ ስማቸው ከገነኑ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ የሚጠራው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡

እግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብርን የሚሰጡ ሁሉ ከነገር እንኳን አንዳች እንደማይጎድላቸው በዘመናት መካከል ተመልክተናል፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚወዱት የሚሆን ጠባቂ በዙሪያቸው ያቆማል። በባቢሎን ምርኮ ሆኖ ስለሕዝቡ የሚያለቅሰውን የነቢዩ ዳንኤልን የጸሎት መልስ ይዞ የመጣው፣ ራእዩንም ያብራራለት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆች ወዳጆች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ወዳጆቻችን፣ ፈጥኖ ደርሶ የሚያድነን አንዱ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን እንዲሁም ሦስቱ እግዚአብሔር የመረጣቸው ጠቢባን ሕጻናት አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤልን ከእሳት ሲያድን ተመለክተነዋል፡፡

ዛሬም ገዳማውያን እናቶችና አባቶቻችን የኃጢአት እቶን፣ የስጋ ፈተና፣ የዲያብሎስ ውጊያ በበረታቸው ጊዜ የሚረዳቸው በመከራቸው ሁሉ ጽናት የሚሰጣቸው እርሱ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እነርሱም በጸሎታቸው ሰዓት ሁሉ ተግተው ይጠሩታል፡፡ የጸሎታቸው በረከት ተካፋይ እንድንሆን ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: