አዲስአበባ ግራንድ ፕሪ አዲስ ለኢትዮጵያ የፈጠረው ሌላኛው ወርቃማ ዕድል

- Advertisement -
Sidebar AD

♦️

♦️ወጣቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ መሀሪ ነጋሽ የአለም አትሌቲክስ ባደረገለት ጥሪ ሀገሩን ወክሎ ወደ ቦትስዋና ዛሬ ተጉዟል

♦️የአለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር መሀሪ ባለ ልዩ ተሰጦ እና በጣም አቅም ያለው ወጣት ሲሉ አመካሽተውታል

♦️በቀጣይስ ወጣቱን ባለሙያ በዓለም አትሌቲክስ በቋሚነት እናየው ይሁን ?

#Ethiopia | የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በታላቅ ስኬት ያከናወነውን አዲስአበባ ግራንድ ፕሪ ውድድር ከነሀስ ወደ ወርቅ ደረጃ ከመሸጋገሩ በተጨማሪ ሌላ ወርቃማ እድል እንደ ሀገር ይዞ ተከስቷል ።

የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ወጣት መሀሪ ነጋሽ በግራንድ ፕሪ እና በተለያዩ የፌዴሬሽኑ ትልልቅ ውድድሮች ባሳየው ብቃት፣አቅም እና ስኬት በአለምአቀፍ ደረጃ ተወዳጅነትንና ተቀባይነትን አግኝቶ ፌዴሬሽኑ ከዚህ በፊት ሲወቀስበት የነበረው በዓለምአቀፍ አደባባይ የተሳትፎ እጥረትን በሰበረ መልኩ በዓለም አትሌቲክስ ጥሪ ተደርጎለት
ዛሬ ጠዋት(ከደቂቃዎች በፊት) ወደ ቦትስዋና ጋቦሮኒ አምርቷል ።

ለወጣቱ ሀላፊ በቀጥታ ከአለም አትሌቲክስ ለዚህ ዕድል ከኢትዮጵያ በብቸኝነት መጋበዙ እዩኝ እዩኝ ሳይል፣ ማንም ሳያየው በጨለማ የተደከመበትን ስራው ፣በዓለም መድረክ ፍሬው መታየት መጀመሩ ለሌሎች ወጣት ባለሙያዎችም በር ከፋች ተደርጎ ተወስዷል።

ከአዲስአበባ እስከ አለም አትሌቲክስ (World Athletics )
በውጤት፣በልፋት እና በነጮች የተሰጠ ታላቅ የተግባር ምስክርነት ማረጋገጫ ሆኖ በተወሠደው በዚህ ዕድል በአቅሙ፣በእውቀቱ እና በስነምግባሩ የተመሰከረለት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ወጣት መሀሪ ነጋሽ የአለም አትሌቲክስ (World Athletics )
እውቅና በመስጠት በአለም አቀፍ ደረጃ በቦትስዋና የሚካሄደውን የዓለም አትሌቲክስ የሚዲያ አካዳሚ ፕሮግራም(World Athletics Media Acadamy Program )ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቦለት ዛሬ(ሠኞ) ንጋት ላይ ወደ ስፍራው አቅንቷል ።

በሚሰራው ስራ በሁሉም የተመሰገነው ወጣት መሀሪ ከአገር ባለፈ፣ የአለም አቀፍ አትሌቲክስ የውድድር ዳይሬክተር ፒርስ ኦካላጋን “ልዩ ተሰጥኦ ያላውና በጣም ጎበዝ የሚዲያ ባለሙያ(Talented
Professional PR and Media Director )”በማለትም በተደጋጋሚ አድናቆት ሲያቀርቡለትና ምስክርነት ሲሠጡለትም ተሠምቷል።

ወጣት መሀሪ ያገኘው እድል እንደ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን እንደ አገርም ኢትዮጵያ በታላላቅ የዓለም የአትሌቲክስ መድረኮች ተወካይ ሳይኖራት መቅረቱ የሚያስቆጭ ቢሆንም አሁን ግን ይሄን ቁጭት የሚያስረሳ የሚመስል ፍንጭ በመታየቱ ሁላችንንም የሚያኮራ ሆኖ ተገኝቷል።

ወጣት መሀሪ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዶ በተጠናቀቀው የአዲስአበባ ግራንድ ፕሪ ውድድር “በዓለም አትሌቲክስ” ተመርጦ የውድድሩ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር በመሆን የመራ ሲሆን በተለይም ውድድሩ ዓለምአቀፍ ስታንዳርድ ይዘት ያለው እንዲሆን እና ስኬታማ እንዲሆን ላደረገው አሰተዋጽኦ በዳይሬክተሩ ተደጋጋሚ እውቅና የተሰጠውና ምስጋና የተቸረው ሲሆን በአለምአቀፍ መድረክም እንዲሳተፍ
አስችሎታል ።

ወጣት መሀሪ በእንደዚህ ዓይነት ትልቅ ምስክርነት በአለም መድረክ እንዲወጡ አቅም እና እውቀት የሚጠይቅ ቢሆንም ነገርግን በሁሉም ዘርፍ ማድረግ እንደሚቻል አሳይቷል ።

ወጣት መሀሪ በተጨማሪም ፌዴሬሽኑ ከሚድያ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት እና ተሳትፎ ከማረጋገጥ ባለፈ፣ፌዴሬሽኑ በውጭ ግንኙነት እና በስፖርት ዲፕሎማሲ የተሻለ አቅም እንዲኖረው እና በአለም አትሌቲክስ ተቀባይነት እንዲያገኝ የተለያዩ
ተግባራት አከናውኗል ።

ቀጣይ የወጣቱ ጉዞ ወዴት ይሁን? የሚለውን …አብረን የምናየው ይሆናል ..የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ግን እንደ መሀሪ አይነት ሰው ማበራከት ይጠበቅበታል ።

ፌዴሬሽኑ ጉዞውን የተሳካ እንዲሆንና ለወጣት መሀሪ ያደረገውን ድጋፍም ከፍተኛ ምስጋና ይገበዋል ።

ወጣት መሀሪ ነጋሽ ከተለያዩ የዓለም አገራት ከተወጣጡ በድምሩ ከ12 ባለሙያዎች አንዱ ሆነህ “ኢትዮጵያ”የሚለውን ታላቅ ስም አንግበህ በዚህ መድረክ በመገኘትህ እና የልፋትህ ውጤት በመሆኑ የሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ዝግጅት ክፍል እንኳን ደስ አለህ ለማለት ይወዳል።

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: