በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ4 ሺህ በላይ የፍቺ ምዝገባ መከናወኑ ተነገረየሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት …

- Advertisement -
Sidebar AD
አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ4 ሺህ በላይ የፍቺ ምዝገባ መከናወኑ ተነገረ
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት  ባለፉት   በዘጠኝ ወራት ውስጥ በወቅታዊ፣ በዘገየ፣ጊዜ ገደቡ ባለፈ ልደት  324,363  የጋብቻ 28,604፣ የሞት 19,448፣  የጉዲፈቻ 278 በአጠቃላይ የአምስቱም ኩነቶች 382ሺ309 አፈፃፀም ምዝገባ  ማድረጉን አስታውቋል ፡፡
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 4452 ወቅታዊ የፍቺ ምዝገባ ተደርጓል ።   ከጤና ተቋማት በሚመጣ የማሳወቂያ ወረቀት የተመዘገበ የልደት እና የሞት 78.04% ምዝገባ በማድረግ የዕቅዱን 84.63% ለማከናወን መቻሉን   የኤጀንሲው  ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።  በሌላ በኩል 142,159 ያላገባ ማስረጃ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን  600,589 ነዋሪዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመመዝገብ አገልግሎት መስጠት ተችሏል።  ከተሰጠው የነዋሪነት መታወቂያ ውስጥ ዲጂታል 99.78%፣ ማኑዋል 0.22%  ማድረስ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
በመጨረሻም የኤጀንሲው  ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ በበጀት ዓመቱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች እና የነበሩትን ጥንካሬዎች በመያዝ በቀጣይ የመጨረሻ ሩብ ዓመት ውስጥ በዕቅድ ተይዘው ያላለቁ ሥራዎችን የሚያጠናቅቅበት  እና ተቋሙ ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው አደረጃጀት የሚገኙ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው በመስራት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ  ይጠበቃል ብለዋል፡፡
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1