17ኛው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል

- Advertisement -
Sidebar AD

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ በነገው ስብሰባው በኢፌዴሪ መንግሥት እና በፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ መካከል የተደረገ የብድር ስምምነት እና በኢፌዴሪ መንግሥት እና በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ማህበር መካከል የተደረገ የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጆችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነ-ምግባር ደንብ አንቀጽ 92 መሰረት፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሠላማዊት ካሳ በምክር ቤቱ ተገኝተው ከአባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች በቃል የሚሰጡትን ምላሽ የሚያዳምጥ ይሆናል።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የሀገሪቱን ዲጂታል ደህንነት ለማጠናከር ያለመውን የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ ይጠበቃል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1