በሻንጣቸው ውስጥ 110 ኪሎ ግራም ካናቢስ የተገኘባቸው የሲሪላንካ መነኮሳት በቁጥጥር ስር ዋሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በሲሪላንካ ዋና ከተማ ኮሎምቦ በሚገኝ አውሮፕላን ማረፊያ 110 ኪሎ ግራም የሚመዝን ካናቢስ በሻንጣቸው ደብቀው የተገኙ 22 መነኮሳት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።

የጉምሩክ ባለሥልጣናት እንደገለጹት እያንዳንዱ መነኩሴ በሻንጣው ውስጥ በልዩ ሁኔታ በተሰራ ድብቅ ክፍል ውስጥ ኩሽ ተብሎ የሚጠራውንና ከፍተኛ ኃይል ያለውን አደንዛዥ ዕፅ አምስት ኪሎ ግራም ያህል ይዞ ተገኝቷል።

አብዛኞቹ ተማሪዎች የሆኑት እነዚህ መነኮሳት የታይላንድ የአራት ቀናት ሙሉ ወጪያቸው የተሸፈነ ጉብኝት አጠናቀው ሲመለሱ ነው የተያዙት።

ጉዞውን አደራጅቷል ተብሎ የሚጠረጠር ሌላ መነኩሴም በኮሎምቦ ከተማ ዳርቻ በቁጥጥር ስር ውሏል።

መነኩሴው ለተጓዦቹ ዕቃዎቹ የእርዳታ ስጦታ እንደሆኑና አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ መኪና መጥቶ እንደሚቀበላቸው ነግሯቸው እንደነበር ፖሊስ ለቢቢሲ ሲንሃላ ገልጿል።

የሀገሪቱ የአደንዛዥ ዕፅ ቁጥጥር ቢሮ በመነኮሳቱ ስልኮች ላይ ባደረገው ምርመራ መነኮሳቱ በቆይታቸው ወቅት የገዳም ልብሳቸውን አውልቀው ሲዝናኑ የሚያሳዩ ምስሎችን አግኝቷል።

መነኮሳቱ አደንዛዥ ዕፁ በትምህርት ቁሳቁሶችና በጣፋጭ ምግቦች ውስጥ ተደብቆ ስለነበር የተሸከሙት ዕቃ ምን እንደሆነ ላያውቁ እንደሚችሉ ፖሊስ ግምቱን አስቀምጧል።

ይህ ክስተት በሲሪላንካ ታሪክ መነኮሳት በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ተጠርጥረው በአውሮፕላን ማረፊያ ሲያዙ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

#srilanka #monks #cannabis #drugtrafficking #crime #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: