#FastMereja I ባሳለፍነው ዓመት በደመቀ ሁኔታ ተጀምሮ የብዙዎችን ትኩረት የሳበው “የታዋቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫል” ለሁለተኛ ጊዜ ሚያዚያ 22 እና 25 ይደረጋል።
ዘንድሮም ከታዋቂው ፔፕሲ (Pepsi) ጋር በመተባበር የሚቀርበው ይህ ታላቅ ስፖርታዊ ድግስ፣ ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ሰዎችን እና የሶሻል ሚዲያ ኮከቦችን በአንድ አረንጓዴ ሳር ላይ ያገናኛል።
ውድድሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ በሚገኘው አዲስ እና ዘመናዊው ኤፍ ቢ (FB) ሜዳ የሚደረግ ሲሆን፦
• ሚያዚያ 22 (ከ8፡00 ሰዓት)፦ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ (ጋዜጠኞች ከ አርቲስቶች፤ ቲክቶከሮች ከድምፃውያን)።
• ሚያዚያ 25 (ከ8፡00 ሰዓት)፦ የፍጻሜው እና የዋንጫ ውድድር።
የዋንጫው ሽሚያ ባለፈው ዓመት ሻምፒዮን የነበሩት ጋዜጠኞች ዋንጫውን ላለማስረከብ ሲፎክሩ፤ አርቲስቶች፣ ድምፃውያን እና ቲክቶከሮች ደግሞ “ዘንድሮ ዋንጫው የኛ ነው!” በሚል ጠንካራ ፉክክር ለማድረግ ተዘጋጅተዋል።
በውድድሩ አሸናፊ የሚሆነው ቡድን የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትለት ሲሆን፣ ከቲኬት ሽያጭ የሚሰበሰበው ገቢ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ተግባራት እንዲውል ይደረጋል።
ሚያዚያ 22 እና 25 በስድስት ኪሎ ኤፍ ቢ ግቢ እንገናኝ!
#CelebrityFootballCup #PepsiEthiopia #SportForCharity
#kidamemedia



Source: FastMereja









No comments yet.