የናፍታ ነዳጅ አቅርቦት ወደ ቀድሞ መጠኑ እንዲመለስ ተወሰነ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት ተከስቶ የነበረውን የናፍታ ነዳጅ አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ፣ የአቅርቦት መጠኑ ወደነበረበት እንዲመለስ መወሰኑን አስታውቀዋል። በዚህም መሰረት በቀን ይቀርብ የነበረው 4.5 ሚሊዮን ሊትር ናፍታ ወደ 9 ሚሊዮን ሊትር ከፍ እንዲል ተደርጓል።

​በመካከለኛው ምስራቅ በተቀሰቀሰው ግጭት ሳቢያ የአቅርቦት ሰንሰለቱ ተቋርጦ የነበረው የናፍታ ነዳጅ፣ አሁን ላይ የምርትና የትራንስፖርት እንቅስቃሴው መሻሻል በማሳየቱ መንግስት ይህንን ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል። ሚኒስትሩ እንደተናገሩት፣ አቅርቦቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ መንግስት በየወሩ ተጨማሪ 20 ቢሊዮን ብር ለነዳጅ ድጎማ የሚመድብ ይሆናል ሲል ፋና ነው የዘገበው።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1