ናፍጣ ወደነበረበት እንዲመለስ ተወሰነ‼️
የናፍታ አቅርቦት መጠን ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት እንዲመለስ ተወሰነ‼️
ናፍታ ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በፊት ወደነበረበት የአቅርቦት መጠን እንዲመለስ ተወስኗል አሉ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ።
አቶ አሕመድ ሽዴ በሰጡት መግለጫ ፥ በአሁኑ ወቅት ያለውን የምርትና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በማየት የናፍታ አቅርቦት ወደነበረበት እንዲመለስ መንግሥት ወስኗል ብለዋል።
በጦርነቱ ምክንያት የናፍታ አቅርቦት በግማሽ ቀንሶ እንደነበር ገልጸው ፥ በዚህም በቀን 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር እንዲቀርብ እየተደረገ ነበር ብለዋል።
አሁን ላይ ግን ከጦርነቱ በፊት ይቀርብ የነበረው በቀን 9 ሚሊየን ሊትር ናፍታ እንዲገባ ተወስኗል ነው ያሉት።
ለዚህም መንግሥት ተጨማሪ 20 ቢሊየን ብር በወር ለነዳጅ ድጎማ እንደሚያደርግ አስገንዝበዋል።
ናፍታው ከጅቡቲ ወደ አዲስአበባ መጓጓዝ ጀምሯል ያሉት ሚኒስትሩ፥አጠቃላይ የነዳጅ ድጎማም ከ300 ቢሊየን ብር ማለፉን ጠቁመዋል።
ቤንዚን እና የአውሮላን ነዳጅ ከጦርነቱ በፊት በነበረው ልክ እየቀረበ እንደሆነ አንስተዋል።
ለአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ ለክልሎች ደግሞ ከነገ ጀምሮ ከጅቡቲ ናፍታ የማጓጓዝ ሥራ እንደሚከናወንም ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.