የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ክፍያን እስከ ሁለት ዓመት በሚደርስ የጊዜ ገደብ ተከፋፍሎ መክፈል የሚያስችል አዲስ አሰራር ይፋ ተደረገ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ለማስገባት የአንድ ጊዜ ክፍያ መፈጸም ለሚከብዳቸው ዜጎች፣ የቆጣሪ ክፍያውን እስከ ሁለት ዓመት በሚደርስ የጊዜ ገደብ መክፈል የሚችሉበትን አዲስ አሰራር ይፋ አድርጉአል።
አገልግሎቱ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የተቋሙ የገበያ ሽያጭና የደንበኞች አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ አቶ ኢሳይያስ ደንድር እንዳስታወቁት፤ አዲሱ አሰራር የተዘረጋው ተቋሙ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት መሠረት በገንዘብ እጥረት ምክንያት የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆን ያልቻሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ነው።
ይህ የአገልግሎት አሰጣጥ በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች የኤሌክትሪክ ኃይል አግኝተው ኑሯቸውን እንዲቀይሩ ያለመ ነው ተብሏል።
አሰራሩም ማንኛውንም አዲስ ኃይል ፈላጊ የህብረተሰብ ክፍል እንደሚመለከት ተገልጿል።
እንደ ስራ አስፈጻሚው ገለጻ፣ ደንበኞች እንደ ምርጫቸው ክፍያውን በየወሩ ከፍጆታ ሂሳባቸው ጋር በጋራ እንዲከፍሉ የሚደረግ ሲሆን፣ የአከፋፈል አማራጮቹም በመግለጫው ወቅት ተዘርዝዋል።
በዚህም እስከ 6 ወር ለሚከፍሉ ያለምንም ወለድ (0%)፣ ከ6 ወር እስከ 1 ዓመት ለሚከፍሉ 3 በመቶ ወለድ፣ ከ1 ዓመት እስከ 1 ዓመት ተኩል ለሚከፍሉ 6 በመቶ ወለድ፣ እንዲሁም፣ እስከ 2 ዓመት ለሚከፍሉ 9 በመቶ ወለድ ታሳቢ ተደርጎ ይስተናገዳሉ ተብሏል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.