የእርጅና ክትባትሩሲያ የሰውነትን እርጅና የሚገታ “ክትባት” እያበለጸገች መሆኑ ገለጸችየሩሲያ ባለሥልጣናት የሰውነትን የእርጅና …

- Advertisement -
Sidebar AD
የእርጅና ክትባት‼️
ሩሲያ የሰውነትን እርጅና የሚገታ “ክትባት” እያበለጸገች መሆኑ ገለጸች‼️
የሩሲያ ባለሥልጣናት የሰውነትን የእርጅና ሂደት ለማዘግየት የሚያስችልና “የእርጅና መከላከያ ክትባት” (Anti-aging vaccine) የሕክምና ዘዴ በማበልጸግ ላይ መሆናቸውን አስታወቁ።
ከመንግሥት ጋር ተባብረው የሚሰሩ ሳይንቲስቶች እንደገለጹት፤ ይህ የሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሕክምና RAGE ተብሎ ከሚጠራውና ከሴሎች እርጅና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ካለው ተቀባይ ዘረመል (Receptor Gene) ጋር የሚቃረን የጂን ሕክምና (Gene therapy) ነው።
በአሁኑ ወቅት የምርምር ሥራው በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ መድኃኒቱ ለሕዝብ ጥቅም እንዲውል እስካሁን ፈቃድ አላገኘም። የዚህ ፕሮጀክት ዋነኛ ግብ የሰዎችን ጤናማ የሕይወት ዘመን ማራዘም ሲሆን፣ እንደ ባለሥልጣናቱ ገለጻ ከሆነ የሕክምናው ውጤት ከ2028 እስከ 2030 ባሉት ዓመታት ውስጥ ለተጠቃሚዎች ሊቀርብ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: