አሜሪካ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸውን ሁለት የኢራን የነዳጅ መርከቦች ልትወርስ ነው
የአሜሪካ መንግስት ባለፉት ሳምንታት በባህር ኃይሏ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሁለት የኢራን የነዳጅ ጫኝ መርከቦችን በቋሚነት ለመውረስ የህግ ሂደት መጀመሩን ብሉምበርግ የዋይት ሃውስ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።
መርከቦቹ M/T Majestic X Phonix በእና M/T Tifani የተሰኙት ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ናቸው።መርከቦቹ የተያዙት ባለፈው ሳምንት በህንድ ውቅያኖስ (በሲሪላንካ አቅራቢያ) ሲሆን፣ ወደ 3.8 ሚሊዮን በርሜል የሚጠጋ የኢራን ድፍድፍ ነዳጅ ጭነው እንደነበር ተገልጿል።
የአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር መርከቦቹን እና ነዳጁን ለዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ገቢ ለማድረግ ክስ መስርቷል። ኢራን ድርጊቱን “የባህር ላይ ዘረፋ” ስትል የጠራችው ሲሆን፣ የአሜሪካ እገዳ የማይቆም ከሆነ “ከባድ ወታደራዊ እርምጃ” እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች።
@seledadotio

No comments yet.