ለሕወሓት ሊተላለፍ የነበረ 18 በርሚል ነጭ ጋዝ
በቁጥጥር ስር ዋለ – የአማራ ክልላዊ መንግሥት
በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ኬላ ላይ በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ፣ በሌሊት ሲንቀሳቀስ የነበረ 18 በርሜል ነጭ ጋዝ የጫነ “ታታ” ተሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። እንደ ክልሉ መንግሥት ገለጻ፣ ይህ ነዳጅ ሕገወጥ በሆነ መንገድ ለህወሃት ሊተላለፍ የነበረ ሲሆን፣ የጸጥታ አካላት ባደረጉት ክትትል ሊያዝ ችሏል።
ይህ ክስተት የተሰማው በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርና በፌደራል መንግሥት መካከል የነዳጅ አቅርቦትን በተመለከተ ውጥረት በነገሠበት ወቅት ነው። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጀነራል ታደሠ ወረደ ከቀናት በፊት እንደገለጹት፣ የፌደራል መንግሥት ወደ ትግራይ ነዳጅ እንዳይገባ ገደብ የጣለው “ህወሃት ለዳግም ጦርነት ዝግጅት እያደረገ ነው” በሚል ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል። ወቅታዊው የነዳጅ ቁጥጥርም የዚሁ የጸጥታ ስጋት ነጸብራቅ እንደሆነ ይነገራል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.