የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ስም ወደ “ትራምፕ” ሊቀየር ነው?
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ በገዛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ያጋሩት ምስል በዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች እና በነዳጅ ገበያው ዘንድ መጠነኛ ድንጋጤን ፈጥሯል።
ነገሩ እንዲህ ነው፤ ባለፈው በፈረንጆቹ ሚያዝያ 29 ቀን ትራምፕ በ”ትሩዝ ሶሻል” ገጻቸው ላይ አንድ ካርታ አጋርተው ነበር። በዚህ ካርታ ላይ ለዓለም ንግድ እጅግ ወሳኝ የሆነውና በኢራን አቅራቢያ የሚገኘው የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ (Strait of Hormuz) ስሙ ተሰርዞ “የትራምፕ ወሽመጥ” ተብሎ ተጽፎ ይታያል።
ምንም እንኳን ይህ ድርጊት በይፋዊ መንግስታዊ ሰነድ የታገዘ ባይሆንም፣ ትራምፕ ይህን መሰል ምስል ማጋራታቸው ብዙዎችን “ለምን?” ብለው እንዲጠይቁ አድርጓል።
ይህ የባህር መስመር ለዓለም ኢኮኖሚ እንደ ደም ስር የሚቆጠር ነው። በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ በርሜል ነዳጅ የሚጓጓዝበት በመሆኑ፣ ጥቃቅን የሚባሉ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እንኳ በነዳጅ ዋጋ ላይ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም አላቸው።
ትራምፕ ይህን ስያሜ የያዘ ካርታ ማጋራታቸው፣ በተለይም በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ፍጥጫ በበረታበት ሰዓት፣ እንደ ትልቅ ትንኮሳ ተቆጥሮባቸዋል።
ብዙዎች ጉዳዩን እንደ ትራምፕ የተለመደ የማስታወቂያ ስራ ቢመለከቱትም፣ የጂኦ-ፖለቲካ ተንታኞች ግን ነገሩን በጥርጣሬ እያዩት ነው። እንዲህ ያለ ስልታዊ ጠቀሜታ ያለውን ቦታ በራስ ስም ለመጥራት መሞከር፣ በቀጠናው ላለው የባህር ላይ ደህንነት እና ለዓለም አቀፍ ንግድ ፍሰት አዲስ ስጋት ሊደቅን ይችላል የሚል ስጋት አሳድሯል።
አሁን ላይ ዓለም እያየችው ያለችው ካርታው በይፋ ይቀየር አይቀየር ሳይሆን፣ ይህ ድርጊት በቀጣይ በሚቀሰቅሰው ዲፕሎማሲያዊ እሰጣ ገባ ላይ ሆኗል ነው የተባለው።
@seledadotio

No comments yet.