በአዲስ አበባ ከተማ እስከ በጀት ዓመቱ ማብቂያ ድረስ የመንግሥት ግዢዎች ታገዱ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ ተቋማት እስከ ሰኔ 30 ድረስ ማንኛውንም አይነት ግዢ እንዳይፈጽሙ መከልከሉ ተነገረ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን እንደገለጹት፤ ይህ ዕገዳ የተጣለው በበጀት ዓመቱ ማብቂያ አራተኛው ሩብ ዓመት ላይ የሚስተዋሉ አላስፈላጊ ወጪዎችን ለመቀነስና የመንግሥትን ሀብት ከብክነት ለመከላከል ነው።

ውሳኔው መሥሪያ ቤቶች የተመደበላቸውን በጀት ያለአግባብ እንዳያባክኑ ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመልክቷል።

ይሁን እንጂ ዕገዳው በመደበኛ የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ተጽዕኖ እንዳይኖረው ልዩ ጥንቃቄ ተደርጓል።

በዚህም መሠረት እጅግ አስፈላጊና መሠረታዊ የሆኑ የግዢ ጥያቄዎች ሲያጋጥሙ ለፋይናንስ ቢሮው በማቅረብና አስፈላጊነቱ ተመዝኖ ልዩ ፈቃድ በማግኘት ግዢ መፈጸም እንደሚቻል ተገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ ከመደበው ዓመታዊ በጀት ውስጥ 72 በመቶ የሚሆነው ለታላላቅ የካፒታል ፕሮጀክቶች መመደቡን ያስታወሰው ቢሮው፤ አዲሱ አሰራር የመንግሥት የፋይናንስ አጠቃቀም በዕቅድ ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዲሆን ያደርጋል ብሏል።

#አዲስአበባ #በጀት #የመንግሥትግዢ #ፋይናንስ #ኢኮኖሚ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: