አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች ተባለ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ የተጣሉት የባህር ላይ እገዳ፣ ኢራን በሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ 4.8 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ገቢ እንድታጣ አድርጓታል።
ካለፈው ሚያዝያ 5 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ በሆነው በዚህ እገዳ ምክንያት 53 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ የጫኑ 31 ታንከሮች በባህር ላይ ቆመው እንዲቀሩ መደረጉን አክሲዮስ ዘግቧል።
እገዳው አሜሪካ በተኩስ አቁም ድርድሮች ላይ እንደ መደራደሪያ ለመጠቀም ባሰበችው ስትራቴጂ ነው። በዚህም እስካሁን ከ40 በላይ መርከቦች መንገዳቸውን እንዲቀይሩ ተገደዋል።
በየብስ ያሉት የነዳጅ ማከማቻዎች አቅማቸው በመሙላቱ ኢራን ያረጁ መርከቦችን እንደ ተንሳፋፊ ማከማቻ ለመጠቀም ብትገደድም፣ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የማከማቻ ቦታው ሙሉ በሙሉ ካለቀ የነዳጅ ጉድጓዶቿን ለመዝጋት ልትገደድ እንደምትችል ተነግሯል።
አንዳንድ የኢራን መርከቦች የአሜሪካን ክትትል ለማምለጥ በፓኪስታንና ህንድ በኩል ረጅም እና ውድ መንገዶችን በመጠቀም ነዳጁን ለቻይና ለማድረስ እየሞከሩ ነው።
ፔንታጎን በበኩሉ እርምጃው ኢራን ሽብርተኝነትን ለመደገፍ የምትጠቀምበትን የገቢ ምንጭ ለመምታት የታለመና ውጤታማ ነው ብሎታል።
@seledadotio

No comments yet.