እርዳታ የሚቀበል ሀገር ሉዓላዊ ነኝ ማለት አይችልም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

- Advertisement -
Sidebar AD

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ‎እርዳታ የሚቀበል ሀገር ሉዓላዊ እና ነጻ ነኝ ማለት አይችልም አሉ፡፡

4ኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተከፍቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በሁሉም መስክ ማምረት ሉዓላዊነትን ያጎናጽፋል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ማምረት ካልቻለች የግብርና ምርትና ሂደቱ በሰዎች በጎ ፈቃድ ላይ መውደቁ አይቀርም ነው ያሉት፡፡

ለምግብ ግብዓት የሚሆኑ የማምረቻ መሳሪያዎች፣ ምርጥ ዘሮች እና ማዳበሪያዎችን በሀገር ውስጥ ማምረት የተሟላ የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ አስረድተዋል፡፡

ነዳጅ እና ጋዝ ማምረት ባለመቻላችን ብዙ ፈተና ገጥሞናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያ ብዙ የነዳጅ እና ጋዝ ሀብት እንዳላቸው ሀገራት ከፍተኛ አቅም ቢኖራትም እስካሁን ድረስ ማምረት ባለመቻላችን ተቸግረናል ሲሉም አብራርተዋል፡፡

21 ትሊየን ሜትሪክ ኪዩብ ጋዝ ያላት ሀገር ያንን ሳታመርት በመቆየቷ ትራንስፖርት እና ኢንዱስትሪው ሊታወክ ችሏል ብለዋል፡፡

በሁሉም መስክ ማምረት ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ መሆኑን በማመን ማቀድ፣ መስራት እና መስፋት ይጠበቅብናል ነው ያሉት፡፡

እርዳታ የሚቀበል ሀገር ነጻ እና ሉዓላዊ ነኝ ማለት አይችልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያዊያን ልመና በቃን እስካላልን ድረስ ጥገኞች ነን ብለዋል፡፡

FBC




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: