ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል የሚወስን መመሪያ ደንብ አለመውጣቱን የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን አስታወቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

ከዚህ በፊት ዝቅተኛ የደሞዝ ወለልን የሚወስን ቦርድ እንዲቋቋም ደንብ ይወጣል ተብሎ የነበር ቢሆንም አስከ አሁን ተግባራዊ አለመደረጉን የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን አስታውቋል።

ዝቅተኛ የደሞዘዝ ወለል እንዲወስን የወጣው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ተግባራዊ እንዲሆን ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ያስታወሱት የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ናቸው።

በጉዳዩ ላይ አሰሪዎች እና የመንግስት አካላትን ለማሳመን በርካታ ስራ መስራቱን ገልፀዋል።

በቂ ወይይት በማድረግ ደንብ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማስገባታቸውን ተናግረዋል።

ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል የሚወሰነው ቦርድ ከመቋቋሙ ባሻገር በአስቸኳይ ጸድቆ የሀገሪቱን ነባረዊ ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ እንዲሰራ ለማድረግ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

#አሐዱ



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: