ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለፕሮፌሰር ድልአየሁ በቀለ እውቅና ሰጡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ኮሌጁ ለ13ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን ባስመረቀበት ወቅት ይፋ እንደተደረገው በሙያቸው በሆስፒታሉ እና በሀገር ደረጃ የእናቶችን ጤና ለማሻሻል ላደረጉት ጉልህ የላቀ ሙያዊ አስተዋጽኦ እውቅና ሰጥቷል፡፡

በሙያቸው የማህጸን እና ጽንስ ሐኪም እና የ በMaternal-Fetal Medicine ሰብ ስፔሻሊት የሆኑት ፕሮፌሰር ድል አየሁ በምርምር ስራቸው ከ120 በላይ የሚሆኑ የጥናት ስራዎቻቸው በስመጥር ዐለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ታትመውላቸዋል፡፡

የእርሳቸውን እውቅና አስመልክቶ የወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው ፕሮፌሰር ድልአየሁ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በትምህርት ክፍል መምህርነት በኃላም የትምህርት ክፍሉ ዋና ሓለፊ ሆነውም ሰርተዋል፡፡

መምህር ብቻ አይደሉም ትውልድን በዕውቀት የሚያንጹ ፡ ተማሪዎቻቸውን ወደ ብቃት አሻጋሪ እና የስራ መሪም እንደሆኑ ተመስክሮላችዋል፡፡ አርሳቸው ያስተማሯዋቸው ሐኪሞች ዛሬ በሀገራችን የጤና ስርአት ግንባር ቀደም ባለሙያ ሆነው እያገለገሉ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ የእናቶችን የሕክምና አገልግሎት በማሻሻል በጤና ሚኒስቴር በተለያዩ ቴክኒካል ቡድኖች ውስጥ በመሳተፍ በሀገር ደረጃ መመሪያዎችን በመዘጋጀት አገልግለዋል፡፡ በማገልገል ላይም ይገኛሉ፡፡በሙያ ማህበራቸው የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ማሕበር ፕሬዝዳንት ሆነውም ሰርተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በቅዱስ ጳውሎስ የስነ ተዋልዶ ጤና እና መብት ኢኒስቲቲዮት ዳይሬክተር ሆነው የእናቶች የጤና አገልግሎት እንዲሻሻል አየሰሩ ይገኛሉ፡፡

በሙያቸው ብዙ ሽልማቶችን ቢቀበሉም ፤ እርካታቸው ግን በሙያቸው ያገለግሏቸው ኃልቁ መሳፍርት እናቶችና ያዳኑት ሕይወት እንዲሁም በእናቶች ጤና ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን ማፍራታቸው ነው፡፡

በእናቶች ጤና ዙሪያ ያበረከቱት ጉልህ አስተዋጽ ለኮሌጁ ባለሙያዎችና በሙያ መስኩ ለሚገኙ ሁሉ ሁነኛ ምሳሌ ናቸው፡፡በሕክምናው ያላቸው ልዩ ብቃት፡ ለእናቶች ጤና እና ልማት ሲውል የላቀ ስኬት እንደሚፈጥር ፕሮፌሰር ድል አየሁን እንደ አብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፕሮፌሰር የእናቶችን ጤና የተሻለ እንዲሆን በእጅጉ እንደሰሩ የኮሌጁ መግለጫ አመልክቷል፡፡

ለፕሮፌሰር ድል አየሁ የተዘጋጀውን ልዩ የላቀ የሙያ አስተዋጽኦ እውቅና ምሰክር ወረቀት ከእለቱ የክብር እንግዳ ከጤና ሚኒስቴርዋ ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ እጅ ተቀብለዋል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: