ኢራን አውሮፓን በከባድ ሚሳኤል ልትመታ እንደምትችል አስጠነቀቀች
የኢራኑ ወግ አጥባቂ የኬይሃን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆሴን ሻሪያትማዳሪ፣ አውሮፓ አገራት የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን የሚያስተናግዱ ከሆነ ኢራን ኢላማ እንደምታደርጋቸው ማክሰኞ ዕለት አስጠንቅቀዋል። አዘጋጁ እንዳሉት፣ አውሮፓውያን የአየርና የባህር ኃይል ሰፈሮቻቸውን ለዋሽንግተን ክፍት ካደረጉ፣ እነዚህ ስፍራዎች በኢራን ጥቃት ሊሰነዘርባቸው የሚችሉ “ህጋዊ ኢላማዎች” መሆን አለባቸው ሲሉ ጽፈዋል።
ሻሪያትማዳሪ አክለውም፣ ኢራን ቀደም ሲል በአረብ ሀገራት ላይ ጥቃት እንደሰነዘረች ሁሉ አውሮፓንም የመምታት አቅም እንዳላት ገልጸዋል። “አውሮፓውያን መንግስታት እኛ መምታት እንደምንችል፣ ያውም በሚገባ መምታት እንደምንችል ያውቃሉ” በማለት የሀገራቸውን ወታደራዊ ዝግጅት አረጋግጠዋል።
እንደ ጋዜጣው ዘገባ፣ አውሮፓ ለኢራን ጥቃት በጣም ተጋላጭ መሆኗንና ጥቃቱን የመቋቋም አቅም እንደሌላት ተጠቅሷል። ይህ ማስጠንቀቂያ የመጣው በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል ያለው ወታደራዊ ውጥረት እየተባባሰ በመጣበትና አውሮፓም በዚህ ግጭት ውስጥ ልትሳተፍ ትችላለች ተብሎ በሚሰጋበት ወቅት ነው።
@seledadotio

No comments yet.