የኢራን ድርድር መሻሻል ማሳየቱን ተከትሎ ትራምፕ በሆርሙዝ ሰርጥ የጀመሩትን ወታደራዊ ዘመቻ በጊዜያዊነት አገዱየአሜሪካው ፕሬዝዳ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የኢራን ድርድር መሻሻል ማሳየቱን ተከትሎ ትራምፕ በሆርሙዝ ሰርጥ የጀመሩትን ወታደራዊ ዘመቻ በጊዜያዊነት አገዱ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር እየተደረገ ያለው ድርድር መሻሻል ማሳየቱን በመጥቀስ፣ በሆርሙዝ ስርጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦችን ለማጀብ ተጀምሮ የነበረው ወታደራዊ ዘመቻ ለጊዜው እንዲቆም ትእዛዝ አስተላለፉ።
“የነፃነት ፕሮጄክት” በሚል መጠሪያ የተጀመረውና በስትራቴጂካዊው ስርጥ በኩል መርከቦችን ለማጀብ የታቀደው ይህ ዘመቻ፣ ለሚደረገው ስምምነት ዕድል ለመስጠት ሲባል ለተወሰነ ጊዜ እንዲቆም መወሰኑን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።
ትራምፕ ይህ ውሳኔ የተላለፈው ፓኪስታንን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት የቀረበላቸውን ጥያቄ መሠረት በማድረግ መሆኑንና ከቴህራን ጋር የሚደረገው ንግግርም ውጤት ሊያመጣ የሚችልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ የጊዜያዊ ዕገዳ ውሳኔ ቢተላለፍም፣ ከግጭቱ ጋር የተያያዘው የባህር ላይ እገዳ አሁንም የቀጠለ መሆኑ የሁኔታውን አሳሳቢነት እና ተለዋዋጭነት የሚያመላክት ሆኗል።
የዓለም አቀፉ የነዳጅ አቅርቦት ከፍተኛ ድርሻ የሚያልፍበት የሆርሙዝ ስርጥ፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ለተፈጠረው ከፍተኛ ውጥረት ማዕከል ሆኖ የቆየ ሲሆን፣ ሁለቱም ወገኖች በመርከቦች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ወይም ሲያስፈራሩ ቆይተዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ እርምጃ ውጥረቱን ከመቀነስ ባለፈ “የመጨረሻ እና የተሟላ ስምምነት” በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሊመጣ እንደሚችል የመፈተሻ ዘዴ ተደርጎ ተወስዷል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: