#Ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ በመጣው ውጥረትና በዓለም አቀፉ የነዳጅ ገበያ ላይ የተደቀነውን ስጋት ተከትሎ፣ የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ቤጂንግ ማቅናታቸው ተሰማ።
ሚኒስትሩ ከቻይናው አቻቸው ዋንግ ዪ ጋር የሚያደርጉት ይኸው ምክክር፣ በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥምር ጥቃት ሳቢያ በነዳጅ ማምረቻ ተቋማት ላይ ጉዳት ደርሶ፣ የዓለም የነዳጅ አቅርቦት መስመር ከፍተኛ መናጋት በገጠመው ወቅት የተደረገ በመሆኑ ልዩ ዲፕሎማሲያዊ ትርጉም ተሰጥቶታል።
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ መሪዎች በዋናነት ቀጣላዊና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች እንዲሁም በጸጥታ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚያደርጉ አመልክቷል። ቻይና በበኩሏ ጉብኝቱ በነገው ዕለት እንደሚከናወን አረጋግጣለች።
ይህ ጉብኝት ኢራን ከምስራቁ ኃያል ሀገር ቻይና ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ ትብብር በማጠናከር፣ በምዕራባውያን የሚሰነዘርባትን ጫና ለመቋቋም እና በነዳጅ ገበያው ላይ የተፈጠረውን አለመረጋጋት በጋራ ለመፍታት የምታደርገው ጥረት አካል ተደርጎ ተወስዷል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#Iran #China #Diplomacy #OilMarket #AbbasAraghchi #MiddleEast #Geopolitics #New
Source: GetuTemesgen








No comments yet.