#Ethiopia | ከ90 ዓመታት በፊት በታሪክ ማህደር ውስጥ ተቀብሮ የቀረው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅርስ ዳግም ለብርሃን በቅቷል፡፡ ለሙዚቃ ወዳጆች፣ ለታሪክ አጥኚዎችና ለባህል ባለሙያዎች ታላቅ የምስራች ይዘን ቀርበናል፡፡
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዋዜማና በጣሊያን ወረራ ወቅት በ1920ዎቹ አጋማሽ በኮሎምቢያ ሪከርድስ አማካኝነት በአዲስ አበባ ተቀድተው የነበሩ 350 የሚጠጉ የሀገር ባህል ሙዚቃዎች ለገበያ ሳይውሉ ለዘመናት ተደብቀው ቆይተዋል፡፡ እነዚህ ውድ ቅርሶች ከራሱ ከቀረጻ ተቋሙ ውጭ በማንኛውም ድርጅት እጅ የማይገኙ ብርቅዬ ሀብቶች ነበሩ፡፡
ይህንን ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረ የሙዚቃ ጉዞ የቱሪን ዩኒቨርሲቲው ምሁር ፕሮፌሰር ጃንፓውሎ ኪያራኮ በጥናት አሰባስበው ለኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በስጦታ አበርክተዋል፡
፡ በአሁኑ ወቅትም ቅርሶቹን ለህዝብ እይታ የሚያበቃ የድምፅና የምስል አውደ ርዕይ ተዘጋጅቷል፡፡
በዚህ ልዩ ዝግጅት ላይ የጥንት አዝማሪዎችንና የባህል ሙዚቀኞችን ድምፅ ማድመጥ የሚቻል ሲሆን የሙዚቀኞቹን ታሪክና ብርቅዬ ፎቶግራፎቻቸውንም መመልከት ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያን የዘመናዊ ሙዚቃ አጀማመር ከምንጩ ለመረዳት የሚያስችል ታላቅ አጋጣሚ ነው፡፡
ሐሙስ ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም
ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ
በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር)
ታሪክን በድምፅና በምስል ለመቃኘት በዚህ ታላቅ አጋጣሚ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡
#ኢትዮጵያ #ሙዚቃ #ታሪክ #ባህል #ወመዘክር #አዲስአበባ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.