#Ethiopia | ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቅርቡ በደንበኞቹ ላይ እየተሞከረ ስላለው አዲስ ዓይነት የማጭበርበር ስልት አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። አጭበርባሪዎቹ የተለያዩ የውጭ አገራት ስልክ ቁጥሮችን በመጠቀም ወደ ደንበኞች ስልክ በመደወልና ወዲያውኑ በማቋረጥ (Missed Call በማድረግ) ደንበኞች መልሰው እንዲደውሉ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።
እንደ ተቋሙ ገለጻ፣ አጭበርባሪዎቹ በብዛት የሚጠቀሙባቸው የዓለም አቀፍ ስልክ ቁጥር መነሻዎች (Prefixes) የሚከተሉት ናቸው፦
+601
+993
+371
+370
+255
+375
+381
ለእነዚህ የማጭበርበሪያ ጥሪዎች መልሰው በሚደውሉበት ወቅት፦
ጥሪው የሚስተናገደው በዓለም አቀፍ ታሪፍ በመሆኑ ከመደበኛው የጥሪ ዋጋ በእጅጉ የላቀ ክፍያ ያስከፍላል።
ይህም ደንበኞችን ለአላስፈላጊ እና ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ይዳርጋል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞቹ ለማያውቋቸው የዓለም አቀፍ ጥሪዎች መልሰው እንዳይደውሉና ራሳቸውን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ ጥብቅ መልዕክቱን አስተላልፏል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#SafaricomEthiopia #ScamAlert #DigitalSafety #Ethiopia #TechNews #Safaricom #ጥንቃቄ #ሳፋሪኮም #ኢትዮጵያ
Source: GetuTemesgen









No comments yet.