#Ethiopia | በኢትዮጵያ የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያን እስካሁን ከ43 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መውሰዳቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርዓያሥላሴ አስታወቁ።
ዳይሬክተሩ ይህንን የገለጹት በኮምቦልቻ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘውን የመታወቂያ አሰጣጥ አፈጻጸም ለመገምገም በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ ነው።
የፋይዳ መታወቂያ ሁሉንም ዜጎች የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ወንጀልን ለመከላከል ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተመላክቷል።
እንደ ሀገር በ2020 ዓ.ም የመታወቂያውን ተጠቃሚዎች ቁጥር 115 ሚሊዮን ለማድረስ ግብ ተቀምጦ እየተሰራ ይገኛል።
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አብዱ ሁሴን በበኩላቸው በክልሉ ለመታወቂያው ስኬታማነት አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
መታወቂያው ከተለያዩ ተቋማት አገልግሎት ጋር እንዲቀናጅ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤቶች እየታዩ መሆኑንም አክለዋል።
በተጨማሪም የፋይዳ መታወቂያ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት የሚደረገውን ጉዞ እንደሚያፋጥነው ተገልጿል።
በደቡብ ወሎ ዞን ብቻ እስካሁን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች መታወቂያውን መውሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣይም ህብረተሰቡን ግንዛቤ በማስጨበጥ ሁሉም ዜጎች የመታወቂያው ባለቤት እንዲሆኑ በትኩረት እንደሚሰራ ተመልክቷል።
#ዲጂታልኢትዮጵያ #ፋይዳ #ብሔራዊመታወቂያ #ኮምቦልቻ #ኢኮኖሚ
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.