ዓለም አቀፍ የእጅ ንፅህና ቀን በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በፓናል ውይይት ተከበረ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በዓለም አቀፍ ደረጃ የእጅ ንፅህና ቀን ሲታሰብ፤ በጤናችን ላይ የሚያመጣው አስገራሚ ለውጥ ተመላክቷል። በትክክለኛ መንገድ እጅን ማፅድዳት በሽታን ከመከላከል ባለፈ የሕይወት አድን ሚናው ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።

​በውይይቱ ላይ ዶ/ር ሄርጎ አበራ እንዳብራሩት፣ እጅን በሳይንሳዊ መንገድ መታጠብ የሚከተሉትን አስደናቂ ጥቅሞች ያስገኛል፦
​የተላላፊ በሽታ ምጣኔን መቀነስ፦ ተላላፊ በሽታዎችን የመተላለፍ ዕድል ከ18% ወደ 2% ዝቅ ያደርጋል።

​የበሽታ መከላከል፦ በንክኪና በፈሳሽ የሚተላለፉ በሽታዎችን በ50% ይቀንሳል።

​መድኃኒት የመለማመድ ችግር፦ በባክቴሪያዎች ላይ መድኃኒት አለመስራት (Drug Resistance) የሚያመጡ በሽታዎችን እስከ 70% ይከላከላል።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ​ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሳይንሳዊውን መንገድ ተከትለው እጃቸውን በተገቢው የሚያፀዱ የጤና ባለሙያዎች 30% ቢሆኑም፣ ይህንን ቁጥር በማሻሻል የሕመምተኞችን ደህንነት ይበልጥ ማረጋገጥ እንደሚቻል ተመላክቷል።

በጤና ተቋማት፣ በምግብ ቤቶችና በሥራ ቦታዎች ንፁህ ውሃ፣ ሳሙናና አልኮልን በበቂ ሁኔታ በማቅረብ እጃችንን የማፅዳት ባህላችንን ካሳደግን፣ ጤናማ ማህበረሰብ መፍጠር እንደምንችል ተመልክቷል።

​እጅዎን በትክክለኛ ቅደም ተከተል በማፅዳት ራስዎንና የሚወዱትን ሰው ይጠብቁ!

“የአገልግሎት ጥራት አርማችን”





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: