ዓላማችን በኳታር ዓለም ዋንጫ መሳተፍ ነው:- አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ዝግጅቱን ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ ወደ ራባት ያቀናል።

ውድድሩ ሊመጀመር የአንድ ሳምንት ዕድሜ ብቻ የቀረው ሲሆን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር 21 ተጫዋቾችን ይዘው ወደ ሞሮኮ እንደሚጓዙ ገልጸዋል። አሰልጣኙ በዚህ ሰዓት ታዳጊዎቹ በተሻለ የሥነ-ልቦና ደረጃ ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

የተጫዋቾቹ መነሳሳትና የቡድኑ አንድነት ለውጤት እንደሚያበቃቸው ያላቸውን እምነት የገለጹት አሰልጣኙ፣ ዋናው ግባቸው ኳታር ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ማለፍ መሆኑን ተናግረዋል።

የተጫዋቾችን ጤንነት በተመለከተም በቡድኑ ውስጥ ምንም ዓይነት አሳሳቢ የጉዳት ዜና እንደሌለና ሁሉም ተጫዋቾች ለውድድሩ ዝግጁ መሆናቸውን አሰልጣኙ አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ባህሩ ጥላሁን፣ እንደ ፍቅሩ ተፈራ እና ሚካኤል ወ/ሩፋኤል ያሉ ባለሙያዎች በአሰልጣኝ ቡድኑ ውስጥ በአዲስ አባልነት መካተታቸውን ገልጸው ይህም ለቡድኑ ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ሞሮኮ፣ ከግብፅ እና ከቱኒዚያ ጋር መደልደሉም ይታወሳል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#EBC #sports #walia


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2