#Ethiopia | በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ወሳኝ የመልስ ጨዋታ ፒኤስጂ ከባየር ሙኒክ ጋር አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
በአሊያንዝ አሬና በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ኡስማን ዴምቤሌ ለፒኤስጂ ቀዳሚዋን ግብ ሲያስቆጥር የባየር ሙኒኩ ሃሪ ኬን በጭማሪ ሰዓት የቡድኑን የአቻነት ግብ አስቆጥሯል።
ሆኖም ፓሪስ ላይ በተደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ 5 ለ 4 አሸንፎ የነበረው ፒኤስጂ በድምር ውጤት 6 ለ 5 በመርታት ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።
የአምናው የሻምፒዮንስ ሊግ ባለክብር ፒኤስጂ በሉዊስ ኤንሪኬ መሪነት በቡዳፔስት በሚደረገው የፍጻሜ ፍልሚያ ከአርሰናል ጋር ለዋንጫ የሚፋለም ይሆናል።
በጨዋታው ላይ የፒኤስጂው ኡስማን ዴምቤሌ ገና በ3ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ለፓሪዚያኑ ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረች ሲሆን የባየር ሙኒኩ ተከላካይ ኡፓሜካኖ በፈጣን የፒኤስጂ አጥቂዎች ሲፈተን አምሽቷል።
ባየር ሙኒክ ጨዋታውን ለመቀልበስ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም የፒኤስጂው ግብ ጠባቂ ድንቅ ብቃት እና የተደራጀው የተከላካይ መስመር የባቫሪያኑን ጉዞ ሊያግዱ ችለዋል።
ግንቦት 22 በሃንጋሪ ፑሽካሽ አሬና በሚካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ፒኤስጂ ዋንጫውን ለማስጠበቅ ሲጫወት አርሰናል ደግሞ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦችን ወክሎ ለበቀልና ለታላቁ ክብር ይፋለማል።
#PSG #BayernMunich #ChampionsLeague #Football #UCL #Arsenal #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.