የልብ ህክምና ለማግኘት አንድ ህፃን ከ3 እስከ 4 ዓመት ወረፋ ይጠብቃል ተባለ በአሁኑ ወቅት ከ6ሺህ በላይ የሚሆኑ ህፃናት የል…

- Advertisement -
Sidebar AD
የልብ ህክምና ለማግኘት አንድ ህፃን ከ3 እስከ 4 ዓመት ወረፋ ይጠብቃል ተባለ
በአሁኑ ወቅት ከ6ሺህ በላይ የሚሆኑ ህፃናት የልብ ህክምና ለማግኘት ወረፋ እየተጠባበቁ መሆኑን የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል አስታዉቋል ።የማዕከሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ህሩይ አሊ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ አንድ ህፃን የልብ ህክምና ለማግኘት ከ3 እስከ 4 ዓመት ወረፋ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል ።
በዚህ ወረፋ የመጠበቅ ሂደት በርካታ ህፃናት ህይወታቸዉ እንደሚያልፍ ተጠቁሟል ።ጥናቶች እንደሚያሳዩት አሁን ላይ ኢትዮጵያ ካላት የህዝብ ቁጥር አንፃር ወደ 24 የሚጠጉ ሆስፒታሎች ያስፈልጋታል የተባለ ሲሆን ከህፃናት ጋር የተያያዘ ያለዉ አንድ ሆስፒታል በመሆኑ ምንም ያህል ብንሰራ በእኛ አቅም ብቻ ችግሩን መፍታት አስቸጋሪ ነዉ ሲሉ አቶ ህሩይ አክለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም የሰዉ ሀይል አቅማቸዉን የማሳደግ ጥረታቸዉን የበለጠ እያገዘ መሆኑን አስታውቋል ።የተለያዩ አጋር አካላት እና ህብረተሰቡ ተባብረዉ መስራት አለባቸዉ ተብሏል ።
በመባ ወርቅነህ
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: