ሰሜን ኮሪያንና ሩሲያን የሚያገናኘው ቁልፍ ድልድይ ግንባታ መጠናቀቁን የሳተላይት ምስሎች አሳዩ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በሰሜን ኮሪያና በሩሲያ ድንበር ላይ የሚገኘውን ቱመን ወንዝን የሚያቋርጠው አዲሱ ስትራቴጂካዊ የጎዳና ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን የሳተላይት ምስሎች ማሳየታቸው ተዘግቧል።

አዲሱ ድልድይ ከዚህ ቀደም ሁለቱን ሀገራት በየብስ ያገናኝ ከነበረውና “የጓደኝነት ድልድይ” ተብሎ ከሚጠራው ነባር የባቡር መስመር ጎን የተገነባ ነው።

የሩሲያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው አዲሱ ድልድይ በቀን እስከ 300 ተሽከርካሪዎችንና 2 ሺህ 850 ሰዎችን የማስተናገድ አቅም አለው።

የሩሲያ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ ድልድዩን ለመገንባት የወጣው ጠቅላላ ወጪ ከ9 ቢሊዮን ሩብል በላይ እንደሆነ ተገምቷል።

ይህ የግንባታ ወጪ በወቅታዊ የምንዛሬ ተመን ሲሰላ 120 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም 88 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ ገደማ ይሆናል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #bbc


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1