የናይጄሪያ ጦር የሰራዊቱ አባላት ማንኛውንም የማኅበራዊ የትስስር ገጽ ከመጠቀም እንዲቆጠቡ ጥብቅ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ተሰምቷል።
የጦሩ አዛዥ ሜጀር ጀነራል ማቲያስ በወታደራዊ ፖሊስ አባላት ስልጠና ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ትዕዛዙን በማያከብሩ ወታደሮች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ይወሰዳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ወታደሮች በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሊኖራቸው እንደማይገባ የገለጹት አዛዡ፣ የየደረጃው የጦር መሪዎች ሰራዊቱ ድርጊቱን እንዳይፈጽም እንዲከታተሉ መመሪያ አስተላልፈዋል።
ዳይሊ ፖስት ናይጄሪያ የዘገበው ይህ መመሪያ፣ ወታደራዊ ስነ-ምግባርን ለማስከበር ያለመ ነው።
#አሐዱ_
Source: Yeneta Tube









No comments yet.