“ኪም ጆንግ ኡን ከተገደሉ ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጥቃት ትሰነዝራለች:-አዲሱ ድንጋጌ‼️
የሰሜን ኮሪያ መንግስት በሕገ መንግስቱ ላይ ባደረገው አዲስ ማሻሻያ፣ መሪው ኪም ጆንግ ኡን በጠላት ሃይሎች ከተገደሉ ወይም የግድያ ሙከራ ከተፈጸመባቸው ወታደራዊ ሃይሉ አውቶማቲክ የሆነ የኒውክሌር አጸፋዊ ጥቃት እንዲሰነዝር አዝዟል።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው የአይሑድ እና የአሜሪካ ጥምረት በቴሕራን ላይ በሰነዘሩት ጥቃት የኢራኑ የበላይ መሪ አሊ ካሜኒ እና የቅርብ አማካሪዎቻቸው መገደላቸውን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።
ኪም ጆንግ ኡንም ተመሳሳይ “የአመራር ማጥፋት” (Decapitation Strike) ጥቃት ሊሰነዘርብኝ ይችላል በሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቃቸው ተነግሯል።
በፒዮንግያንግ በተካሄደው 15ኛው የሰሜን ኮሪያ የሕዝብ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ በጸደቀው የኒውክሌር ፖሊሲ ሕግ አንቀጽ 3 ላይ እንደሰፈረው፣ የአገሪቱ የኒውክሌር ሃይል ዕዝ እና ቁጥጥር ስርዓት በጠላት ሃይሎች ጥቃት አደጋ ላይ ከወደቀ፣ የኒውክሌር ጥቃት “በአውቶማቲክ መንገድ እና ወዲያውኑ” ይፈጸማል።
ይህ ማለት መሪው ኪም ጆንግ ኡን ትዕዛዝ መስጠት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ቢሆኑ ወይም ቢገደሉ፣ ወታደራዊ መኮንኖቹ ያለምንም ተጨማሪ ትዕዛዝ አጸፋውን እንዲመልሱ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።
@seledadotio

No comments yet.