…
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ፤
ያንጎ ግሩፕ፣ ከ6 የአፍሪካ ሀገራት እና ከ600 አመልካቾች ውስጥ የተመረጡ 24 የ2026 የያንጎ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ተሳታፊዎችን ይፋ አደረገ! የተመረጡት ተሣታፊዎች፣ በ12 ሳምንታት ውስጥ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መሠረት ያላቸው ፕሮጀክቶችን የቴክኒክ ክሂላቸውን በመጠቀም የሚያዘጋጁ ሲሆን በመጨረሻ በአቢጃን በሚካሄደው ልዩ ዝግጅት ላይ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
የተመረጡት ተሳታፊዎች ከኮት ዲቯር፣ ዛምቢያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሴኔጋል፣ ሞዛምቢክ እና ጋና የመጡ ሲሆን፣ ፕሮግራሙ ተሣታፊዎቹን በያዝነው የሥራ ዓመት ከ2 ሀገራት ወደ6 በማሳደግ ተደራሽነቱ መጨመሩን አስመስክሯል፡፡
የዘንድሮው ፕሮግራም በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI) ተግባራዊ አጠቃቀም ላይ ያተኩራል። ተሳታፊዎችም እንደ የጤና ዕውቀት ማበልጸጊያ መሣሪያዎች፣ የኃይል ክትትል ሥርዓቶች፣ የትራፊክ ማሻሻያ ሞዴሎች እና በአካባቢ ቋንቋዎች ላይ የተመረኮዙ የትምህርት መፍትሔዎችን ገንብተው እንደሚያሳዩ ይጠበቃል።
ፌሎውሺፑ በሦስት ደረጃዎች የተዋቀረ ነው፡፡ እነሱም፡- ዘላቂ መፍትሔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችን መለየት እና የገበያ ትንተና፣ የምርት ልማትና ዕድገት እና የመጨረሻ አቀራረብ። ፕሮግራሙ በ“ዴሞ ደይ” ወይም ተሣታፊዎች የተዘጋጁበትን ካቀረቡ በኋላ ይደመደማል፡፡ በዚህ ቀን፣ ቡድኖች ፕሮጀክቶቻቸውን ለኢንዱስትሪ ባለሙያዎች እና አጋሮች የሚያቀርቡ ሲሆን ሥራቸው ተስፋ እንዳለው ከታመነበት፣ የሥራ ማስጀመሪያ ፋይናንስ ድጋፍ (seed funding) ሊያገኙ ይችላሉ።
“የንጎ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም፣ በአካባቢያዊ የቴክኖሎጂ ሥነምኅዳር ላይ ያቀድነው የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንታችን አካል ነው።” ያሉት የያንጎ ግሩፕ ዋና የንግድ ጉዳዮች ኃላፊ አዴኒዪ አዴባዮ፣ አክለውም “በቴክኖሎጂው ዘርፍ ላይ በመሰማራት ላይ ያሉ ባለተሰጥኦ ተሳታፊዎችን በመደገፍ እና በተለያዩ ገበያዎች መካከል የሥራ ትብብርን በመፍጠር፣ በአፍሪካ ገበያዎች ያሉ የቴክኖሎጂ ፍላጎቶችን የሚፈቱ የዘላቂ መፍትሔዎች ልማት ላይ ለመሳተፍ እንፈልጋለን፡፡ ጎን ለጎንም፣ አዳዲስ ሐሳብ አመንጪዎች ከአንድ ሀገር በላይ ሊሠሩ የሚችሉ ምርቶችን እንዲገነቡ እና እንዲያሳድጉ የመርዳት ከፍተኛ ፍላጎት አለን።” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
እንደ ዓለም ባንክ ገለፃ፣ አፍሪካ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሒሳብ (STEM) ባለሙያዎች እጥረት አጋጥሟታል። በመሆኑም፣ ፕሮግራሙ በባለሙያዎች ምክር እና በተግባራዊ የፕሮጀክት ሥልጠና መሠረትነት ላይ ተመርኩዞ ተሳታፊዎችን በተግባር ወደቴክኖሎጂና ዕውቀት ልምምድ በማቅረብ፣ ወደ ቴክኖሎጂ ሙያዎች የሚያመሩትን የዕውቀት መንገዶች በሙሉ ማጠናከር ይፈልጋል።
በቀደሙት ፕሮግራሞች እና ልምድ ልውውጦች ውስጥ፣ ተሳታፊዎች በጤና፣ በትምህርት እና በምህንድስና መስኮች የተለያዩ መፍትሔዎችን አበርክተዋል። አንዳንድ የፕሮግራሙ ተመራቂዎች በአጋር ድርጅቶች ውስጥ ቀጣይነት ያላቸውን የልምምድ ሥራዎች (internships) ያገኙ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ማኅበረሰብ ለሚጠቅሙ ፕሮጀክቶቻቸው እውን ማድረግ የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ ተቀብለዋል። የአልሙናይ አባላትም ከፌሎውሺፑ በኋላ አዳዲስና ጀማሪ ኩባንያዎችን፣ ዲጂታል ምርቶችን እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ማኅበረሰብ ተኮር ፕሮጀክቶችን በመጀመር ሥራቸውን ቀጥለዋል።
– – –
ስለያንጎ ግሩፕ
ያንጎ ግሩፕ፣ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ዘመን አፈራሽ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ዕለታዊና ኑሮን የሚያቀሉ አገልግሎቶች በመቀየር ማኅበረሰቦችን የሚያገለግል ተቋም ነው። ለፈጠራ ባለው የማያወላውል ቁርጠኝነት፣ ከዓለም ዙሪያ መሪ ቴክኖሎጂዎችን ወደተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያለምንም እንከን ወደ የተቀናጀ የዕለት ተዕለት አገልግሎቶች ይቀይራል፤ በየጊዜውም ያዘምናል፡፡
የያንጎ ግሩፕ፣ የትራንስፖርት፣ የማድረስ፣ የፉድቴክ፣ የመዝናኛ እና ሌሎች ዲጂታል አገልግሎቶቹን በአፍሪካ ውስጥ ባሉ ከ30 በላይ ሀገራት፣ በላቲን አሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በደቡብ እስያ እና ሌሎች የዓለም ሀገራት ውስጥ ይሰጣል።
ለተጨማሪ መረጃ: pr@yango.com. ላይ ይጎብኙን፡፡



Source: FastMereja









No comments yet.