የኢራን ዩራኒየም ካልጠፋ ጦርነቱ አያበቃም

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ ባሻገር መላውን ዓለም ሊያሳስብ የሚችል ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰንዝረዋል።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ እስራኤል ከኢራን ጋር የገባችበት ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ “መቋጫ አግኝቷል” ብሎ ማሰብ ስህተት ነው።

​ኔታንያሁ ለሲ.ቢ.ኤስ (CBS) «60 Minutes» ፕሮግራም በሰጡት ቃለ-መጠይቅ፣ የጦርነቱን ማብቂያ ከአንድ ወሳኝ ቅድመ-ሁኔታ ጋር አያይዘውታል። ይህም በኢራን እጅ የሚገኘው የበለጸገ ዩራኒየም ሙሉ በሙሉ መወገድ ነው።

የቴህራን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ለቀጠናው ብቻ ሳይሆን ለእስራኤል ህልውና ቀዳሚው ስጋት መሆኑን ገልጸዋል።

ምንም እንኳን የተለያዩ የተኩስ አቁም ጥረቶች ቢኖሩም፣ እስራኤል ግን መከላከያዋን ከማጠናከርና ለጥቃት ከመዘጋጀት ወደኋላ እንደማትል አስታውቀዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢራን ላይ የሚደረገውን ጫና እንዲያበረታታና የኒውክሌር ምኞቷን እንዲገታ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

​ይህ የኔታንያሁ ንግግር የመጣው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ወታደራዊ ፍጥጫ ወደ አደገኛ ደረጃ በተሸጋገረበት እና ቀጠናዊ አለመረጋጋት በጨመረበት ወቅት ነው።

እስራኤል “ጦርነቱ አልተቋጨም” ማለቷ፣ ወደፊት በኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ ሊሰነዘሩ ለሚችሉ እርምጃዎች እንደ መንደርደሪያ ሊታይ ይችላል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#እስራኤል #ኢራን #ኔታንያሁ #ኒውክሌር #መካከለኛው_ምስራቅ #ዜና #ዓለም_አቀፍ_ፖለቲካ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: