#Ethiopia | የአዲስ አበባን የከተማነት እድገት ታሪክ እና በአሁኑ ወቅት እየተከናወኑ ያሉ ዘመናዊ የልማት ስራዎችን መሰረት ያደረገ ልዩ የውይይት መድረክ ነገ እንደሚካሄድ ተነገረ።
መድረኩ የከተማዋን ያለፈ ጉዞ ከመዳሰስ ባለፈ አሁን ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ መሰናክሎችን እንዲሁም የአለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በስፋት ለመመልከት ያለመ ነው።
የናሽናል ሚዲያ አክስዮን ማህበር ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘካርያስ ብርሃኑ እንደገለጹት ኤንቢሲ ኢትዮጵያ በመንግስትና በህዝብ መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ ለማገልገል ካለው እቅድ አንጻር ይህንን መድረክ አዘጋጅቷል።
በመሆኑም በከተማዋ ሁለንተናዊ ለውጥ ላይ የሚመለከታቸው አካላት በጋራ በመምከር የድርሻቸውን እንዲወጡ ማስቻል የውይይቱ ዋነኛ ግብ መሆኑን አስረድተዋል።
በዚህ ዝግጅት ላይ የከተማ ልማት ባለሙያዎች፣ የዘርፉ ምሁራን፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና የኪነጥበብ ሰዎች የሚሳተፉ ሲሆን አንጋፋ ምሁራንም በመወያያ ነጥቦች ላይ መነሻ ጽሁፍ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።
ውይይቱ ነገ ማክሰኞ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት በአድዋ ድል ሙዚየም ሁለገብ አዳራሽ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ30 ጀምሮ የሚከናወን ሲሆን ታዋቂ ግለሰቦችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችም እንደሚገኙ ተመላክቷል።
#አዲስአበባ #የከተማልማት #ውይይት #ልማት #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.