በኢትዮጵያ የተመዘገቡ ስኬቶች የመንግሥትና የሕዝብ የጋራ ቁርጠኝነት ውጤቶች ናቸው – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮጵያ የተመዘገቡ ስኬቶች የመንግሥትና የሕዝብ የጋራ ቁርጠኝነት ውጤቶች ናቸው አለ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።

አገልግሎቱ ‘ቃል በተግባር! ኢትዮጵያ እያከናወነች ነው!’ በሚል መሪ ሀሳብ ባወጣው መግለጫ፤ የተመዘገቡት ስኬቶች ኢትዮጵያ በትክክለኛ የልማትና የዕድገት ጎዳና ላይ መሆኗን የሚያረጋግጡ ናቸው ብሏል።

በዚህም ኢትዮጵያ በዜጎች ሕይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ የሚመጣበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ መድረሷን ገልጿል።

አገልግሎቱ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

ቃል በተግባር !
ኢትዮጵያ እያከናወነች ነው!

ኢትዮጵያ በተለያዩ የልማት ዘርፎች የጀመረቻቸው ግዙፍ ተግባራት የትውልድ ተስፋ ከመሆን ባለፈ፣ በተጨባጭ ስኬቶች የታጀቡና ቃል በተግባር የተፈጸመባቸው ድሎች ሆነዋል።

በግብርናው ዘርፍ፣ በተለይም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የታየው ዐቢይ ለውጥ ሀገሪቱን ከውጪ የዕርዳታ ስንዴ ጥገኝነት አላቆ ራስን ወደ መቻል ከፍ አድርጓታል። ምርቱን ለውጭ ገበያ ማቅረብ (ኤክስፖርት) መጀመሯም፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ትግል ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሮታል።

በኢንዱስትሪው መስክ የውጭ ምንዛሬ ፍሰትን ለመታደግ የተወጠነው “የተኪ ምርቶች ንቅናቄ”፣ የኢንዱስትሪ ግብአቶችንና የፍጆታ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ በማምረት ረገድ ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። ይህም ሀገራዊ ምርታማነትን በማነቃቃት የኢኮኖሚውን መዋቅር እያጠናከረ ነው።

የከተሞችን ገጽታ ለማሻሻልና ለዜጎች ክብር ያለው ሕይወት ለመስጠት የተጀመረው የኮሪደር ልማት፣ አዲስ አበባን እና የክልል ከተሞችን የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዳረሻ ከማድረግ ባለፈ፣ ምቹ የመንቀሳቀሻ መንገዶችንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሠረተ ልማቶችን እውን በማድረግ ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ላይ አዲስ ተስፋ እንዲሰንቁ አድርጓል።

የኢትዮጵያዊያን የጋራ ትብብር ማሳያ በሆነው በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ኢትዮጵያ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በሚደረገው አለም አቀፍ ጥረት ቀዳሚ ከሆኑ አገራት ተርታ እንድትሰለፍ ያደረገ የማይደበዝዝ አሻራ ማኖር ትችሏል።

ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማደስ ፣ አዳዲስ መዳረሻዎችን በመገንባት እና የንጹህ ኢነርጂ ኢንቨስትመንቶችን በማስፋፋት ሀብቶች እንዲለዩ እንዲገለጡ እና የኢኮኖሚ መሰረት እንዲሆኑ የተሰራው ወሳኝ ሥራ ፍሬው የሚታይበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ይገኛል፡፡

እነዚህ ስኬቶች የመንግሥትና የሕዝብ የጋራ ቁርጠኝነት ውጤቶች ናቸው። ኢትዮጵያ በትክክለኛ የልማትና የዕድገት ጎዳና ላይ መሆኗን የሚያረጋግጡ ከመሆናቸውም በላይ በዜጎች ሕይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ የሚመጣበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ መድረሳችንን ያሳያሉ።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1