አዋሽ ኢንሹራንስ “የደንበኞች ሳምንት” ተጀመረ።

- Advertisement -
Sidebar AD

​#Ethiopia | አዋሽ ኢንሹራንስ “የላቀ ቁርጠኝነት ለላቀ አገልግሎት” በሚል መሪ ቃል ዓመታዊ የደንበኞች ሳምንት አስጀምሯል።

ክብረ በዓሉን ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መስሪያ ቤት በደመቀ ሁኔታ አስጀምሯል።

ኩባንያው ክብረ በዓሉን ምክንያት በማድረግ እስከ 25 በመቶ የሚደርስ የዋጋ ቅናሽ እና ነባር የኢንሹራንስ ሽፋን ማሻሻያዎችን ለደንበኞቹ ይፋ አድርጓል።

​በክብረ በዓሉ መክፈቻ ላይ የአዋሽ ኢንሹራንስ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ገመዳ እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጅባት አለምነህ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኩባንያው ከደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን እና አስተያየቶችን ለመቀበል 9696 የተሰኘ ነጻ የጥሪ ማዕከል አገልግሎት ላይ ማዋሉን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር የዲጂታል የጉዞ ኢንሹራንስ አገልግሎት መጀመሩን እንደ ማሳያ ጠቅሰው፣ በቅርቡም የደንበኞችን እንግልት የሚቀንስ አዲስ ዲጂታል ቻናል ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

​በዚህ የደንበኞች ሳምንት ኩባንያው ለደንበኞቹ ያዘጋጃቸው ዋና ዋና ጥቅማጥቅሞች መካከል በቤት መግዣ ብድር ፣ በግል የህይወት ኢንሹራንስ፣ በትምህርት፣ በሠራተኞች ካሳ እና በድንገተኛ አደጋ የኢንሹራንስ አይነቶች ላይ ለአንድ ወር የሚቆይ የ25% ልዩ ቅናሽ ተደርጓል።

አጠቃላይ የሞተር ኢንሹራንስ ሽፋን ላላቸው ደንበኞች፣ ቀደም ሲል የነበረው የ200,000 ብር የንብረት ውድመት ካሳ ያለ ተጨማሪ ክፍያ ወደ 300,000 ብር እንዲያድግ ተደርጓል።

ለሶስተኛ ወገን ሞትና አካል ጉዳት የሚከፈለው የካሳ መጠን ከ250,000 ብር ወደ 350,000 ብር ከፍ እንዲል ተወስኗል።

በማህበራዊ ሚዲያ (ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ኤክስ እና ኢንስታግራም) በሚደረጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄዎች ላይ ለሚሳተፉ ደንበኞች የተለያዩ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል።

​ይህ የደንበኞች ሳምንት በሁሉም የኩባንያው ቅርንጫፎች ለተከታታይ ሰባት ቀናት በተለያዩ ስፖርታዊና ማህበራዊ ሁነቶች ታጅቦ የሚቀጥል ሲሆን፣ ደንበኞች በቅርንጫፎች በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: