የዓለም አትሌቲክስ ከፍተኛ አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የዓለም አትሌቲክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጆን ረጂዮን እና የውድድሮችና ሁነቶች ዳይሬክተር ማርክ ሀስት ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል።

አመራሮቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን እና ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ይህ የአመራሮቹ ጉብኝት ኢትዮጵያ ከዓለም አትሌቲክስ ጋር የጀመረችውን የስፖርት ዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ታምኖበታል።

በቆይታቸውም ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የአደይ አበባ ስታዲየምን እና የተለያዩ የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ የ2028 የዓለም አትሌቲክስ አልቲሜት ሻምፒዮናን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ለዓለም አትሌቲክስ ጥያቄ ማቅረቧ ይታወሳል።

#አትሌቲክስ #ስፖርት #ኢትዮጵያ #አዲስአበባ #የዓለምአትሌቲክስ #athletics #sports #worldathletics #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: